RD Manual MKHN
RD Manual MKHN
:
ኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበር OP/KTSC/044
KOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY
ማንዋል . Page No.:
Issue No
1 Page 1 of 1
የምርምርና ስርፀት
አሰራር መመሪያ ማንዋል
አዘጋጆች
ንጉሴ ሙላት
ከድር ዘዉዱ
መሰረት ገነቱ
ሕይወት ይመር
ህዳር 2005 ዓ.ም
1 Page 1of 2
ክፍል 1
i. መግቢያ--------------------------------------------------------------------------------------------1
1 Page 2 of 2
4.1 የጥናት መረጃ ማጠናቀሪያ ስልት አይነቶች-----------------------------------------------------14
ክፍል 2
1.1 ትርጉም---------------------------------------------------------------------------------------------
24
ክፍል 3
1.ሪፖረት አቀራረብ-----------------------------------------------------------------------------------------
44
1 Page 1 of 47
i. መግቢያ
ምርምርና ስርፀት በአንድ ድርጅት ዉስት ወጭ ቆጣቢና ዉጤታማ አሰራር እንዲኖር ፤ ዉጤታማ ያልሆኑ አሰራሮች እንዲቀየሩ፤አዳዲስና ከዘምኑ
ቴክኖሎጂ ጋር አብረዉ ሊሄዱ የሚችሉ አሰራሮች በድርጅቱ እንዲተገበሩና አዳዲስ የፈጠራ ሃሳቦችና፤ችግሮችን መፍታት የሚያስችሉ ጥናቶችና
ፕሮጀክቶችን በመስራት ድርጅቱን ወደተሻለ ምእራፍ ለማሸጋገር ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡ በኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበርም ምርምርና
ስርፀት በአገልግሎትና አሰራር ማሻሻያ አገልግሎት ስር በዋና ክፍልነት ተዋቅሮ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን ፡፡ የምርምርና ስርፅት ወሳኝ
ተግባራትን ለማከናወን የምርምርና ስርፀት አሰራር መመሪያ ማንዋል መኖሩ ለአሰራር አስፈላጊ በመሆኑ የህ ማንዋል ተዘጋጅቷል፡፡አንድን
ፕሮጀክት ወይም ጥናት ለመስራት ጥናቱ ወይም ፕሮጀክት ፡-
1 Page 2 of 47
ክፍል አንድ
ጥናት (reaserch)
1 Page 3 of 47
ምእራፍ 1
የጥናት ፕሮፖዛል ማለት አንድ አጥኚ ለመስራት ላቀደው ስራ የሚያቀርበው ሰነድ ሲሆን፤ ጥናቱ/ስራው/ ምን
እንደሆነ፤ለምን፤ እንዴት፡ የት፤ መቸ፤ እና ለማን እንደሚሰራ የሚገልፅ ነው፡፡
1.2 የጥናት ፕሮፖዛል ጥቅም (Importance of Research proposal)
የጥናት ፕሮፓዛል መፃፍ በርካታ የተለያዩ ጠቀሜታዎች ይሰጣል፡፡ ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
1 Page 4 of 47
አንድ የጥናት ፕሮፖዛል ከመቀረፁ በፊት ግልፅ የሆነ የጥናት መነሻ ያስፈልጋል ፡፡ አንድ አጥኝ እነዚህን
ጥያቄዎች ከተለያዩ ቦታዎች ሊያገኝ ይችላል፡፡ ለምሳሌ
i. ከአካባቢ ምልከታ(observation)
አጥኝዎቹ ብዙዉን ጊዜ አካባቢን አትኩረዉ ስለሚመለከቱ በዙሪያ ያለዉን ችግር በቀላሉ መለየት ይችላሉ፡፡
1 Page 5 of 47
1 Page 6 of 47
X. የተዛማጅ ፅሁፍ ምልከታ(Litrature Review)፡- የተዛማጅ ፅሁፍ ምልከታ በሚጠናው ጥናት ዙሪያ ከዚህ
በፊት በተጠኑ ጥናቶችን፤ ስምምነቶችን የተቀመጡ ንድፈ ሃሳቦችን በጥልቀት የምናይበት ቦታ ነው፡፡
ይህ ክፍል ጥናት በሚደረግበት ርእስ ዉስጥ የሚገኙትን ቁልፍ ቃላትን በመያዝ የተለያዩ የመረጃ መረቦችን በማሰስ
በጥናቱ ዙሪያ የተጻፉ መረጃዎችን በመፈለግ ዋቢ መረጃ ማዘጋጀት አለበት፡፡
በተቻለ መጠን አጥኝዉ ከተዛማጅ ጽሁፍ ፍሬ ነገሩን በማስታወሻ በሚያሠፍርበት ጊዜ በራሱ ቃላት /ቋንቋ/ ቢጠቀም
ይመረጣል ፡፡ነገር ግን በአንድ ተዛማጅ ጽሁፍ ዉስጥ አጥኝዉ የሚያገኘዉ ፍሬ ነገር አገላለጹ በጣም ማራኪ ከሆነበትና
በራሱ ቃላት/ቋንቋ/ ቢያስቀምጠዉ ፍሬ ነገሩ ለዛዉን የሚጣ ከሆነ እንዳለ ወስዶ ሊጠቀምበት ይችላል ፡፡
በጥናቱ ርዕስ ዙሪያ ከአሁን በፊት የተሰራ ስራ ካለ፤ የነበሩት ቁልፍ ፅንሰ ሃሳቦች ምን እንደሆኑ፤ በርዕሱ ዙሪያ
ሙህራኖች የተስማሙበት ንድፈ ሃሳብ ምን እንደሆነ፤ በየትኛው የርዕሱ ፅንሰ ሃሳብ ላይ ትኩረት እንደተደረገ፤ ጥናቱ
ሲካሄድ የተከተሉት ዘዴ ወይም ስልት ምን እንደነበር፤ በተሰሩት ጥናቶች ልዮነቶች መኖራቸውንና አለመኖራቸውን
በተጨማሪም የትኛው የተሻለ እንደሆነ፤ የቅርብ ጊዜ የተሻለ ጥናት መኖሩን፤ አሁን እየተጠና ያለው ጥናት
ከበፊተኞቹና አሁን ካሉ ሌሎች ጥናቶች የሚለየው ምን እንደሆነ መመለስ አለበት፡፡
LOGO Form No.:
ኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበር OP/KTSC/044
KOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY
ማንዋል . Page No.:
Issue No
1 Page 7 of 47
በአጠቃላይ የተዛማጅ ፅሁፍ ምልከታ ስፋት በጥናቱ ርዕስና በአጥኝዎቹ የሚወሰን ቢሆንም የፅሁፉ ምዕራፍ እስከ 20
ገፅ ሊደርስ ይችላል፡፡ ነገርግን ለትንንሽ ስራዎች በተወሰኑ ገፆች ሊገለጽ ይችላል፡፡
XI. የጥናቱ ዘዴና አካሄድ (Methodology of the study):- በዚህ ርእስ ስር ሶስት መሰረታዊ ጥያቄዎች ሊመለሱ
ይገባል፡፡ እነሱም “እንዴት?” “መቼ?” እና “ለምን?” የሚሉት ናቸዉ፡፡ ‘’እንዴት’’ የሚለውን ለመመለስ በምን
መልኩ ጥናቱ እንደሚካሄድ ጥልቅ የሆነ ማብራሪያ መስጠት ይኖርበታል፡
‘’መቼ’’ ለሚለዉ ደግሞ የሚሰሩት ስራዎች የአሰራር ዘዴያቸውንና የሚያስፈልጋቸውን የጊዜ ገደብ በተጨባጭ መግለፅ
ይሆናል፡፡
‘’ለምን’’ የሚለውን ለመመለስ የተጠቀምንባቸውን መንገዶች የተለዮ ወይም አዲስ መሆናቸውንና መንገዶቹ የተመረጡበት
ምክንያት ምን እንደሆነ ማረጋገጥ አለበት፡፡
XII. የስራ ዕቅድ(work plan)
1. የጊዜ ሰሌዳ (Time scheduele)
ጥናቱ መቼ ተጀምሮ መቼ እንደሚጠናቀቅ እና ዝርዝር የስራ ክንውኖቹን ከሚፈፀሙ ጊዜ ጋር ያመለክታል ይህም
በሰንጠረዥ ቢገለፅ የተሻለ ግልፅና የጥናቱ ንድፍ ለሚቀርብበት አካል ግልፅ የሆነ መረጃ ይሰጣል፡፡
2. የሃብት ክፍፍል(Budget scheduele)
ለጥናቱ ከሚያስፈልጉት ነገሮች ውስጥ በእጅ ያለውን፤ መገዛት ያለበትን እና ጥናቱ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ
የሚሰራ ከሆነ ወጪው መካተት አለበት፡፡በአጠቃላይ በዚህ ርዕስ ስር ለጥናቱ የሚያስፈልገዉ ወጭ በግልጽ
መቅረብ አለበት፡፡ ይህም በሰጠረዥ ቢቀርብ የተሻለ ግልፅና የጥናቱ ንድፍ ለሚቀርብለት አካል ግልፅ የሆነ
መረጃ ይሰጣል፡፡
XIII. ማጣቀሻ(Reference)
ይህ ርዕስ የጥናቱን እውነተኛነት ያመላክታል፡፡የተጠቀምንባቸዉን የመረጃ ምንጮች፤ በማን እንደተፃፈ፤ መቼ
እንደፃፈ የመረጃ መረቡ ስም በግልፅ መቀመጥ አለበት፡፡
LOGO Form No.:
ኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበር OP/KTSC/044
KOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY
ማንዋል . Page No.:
Issue No
1 Page 8 of 47
ምዕራፍ 2
ጥናት ለችግሮች መፍትሄ በማመንጨት ላይ የሚያተኩር ስራ ነው፡፡ በማንኛውም የሥራ ሂደት የተለያዮ ችግሮች ሊያጋጥሙ
ይችላሉ፡፡ እነዚህንም በአግባቡ በሳይንሳዊ መንገድ በመለየትና በመተንተንለችግሮች አስተማማኝ መፍተሄ ማበጀት
የጥናት ዋና ተግባር ነው፡፡ ስለዚህ ጥናት ሳይንሳዊ ሂደትን የሚከተልና በምልከታና ሙከራ ሊረጋገጡ የሚችሉ ጉዳዮች
ብቻ የሚዳስስ ነው፡፡
የአንድ ጥናት ሥራ ከመጀመሩ በፊት ጥናቱ ለምን፤ እንዴት፤ መቼ፤ ለማን እንደሚሰራ በጥናቱ ፕሮፖዛል ላይ መነደፍ
ይኖርበታል፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት በቅድሚያ በጥናቱ ፕሮፖዛል ላይ የሚታዮ ቢሆንም ጥናታዊ ፅሁፉ ሲዘጋጅም
አብረው መካተትይኖርባቸዋል፡፡
በአንድ ሁኔታ ወይም ችግር ላይ ጥናት ማካሄድ የሚያስፈልገው ሁኔታው ወይም ችግሩ በሚከተለው አኳኋን ሲገኝ ነው፡፡
1 Page 9 of 47
አንድ አጥኚ በአንድ ችግር ወይም ሁኔታ ላይ ጥናት ለማካሄድ በሚያስብበት ጊዜ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የሚከተሉትን ነጥቦች
ማጤን ይኖርበታል፡፡
ጥናት ሊካሄድበት የታሰበበት ችግር አዲስ ነው ወይስ አይደለም ካልሆነስ ምን ያህል ጥናት ተደርጎበታል
የተደረገውስ ጥናት ምን ያህል ስፋትና ጥልቀት አለው?
ጥናት ሊካሄድበት የታሰበበት ችግር በሳይንሳዊ የጥናት ሥልትና በተጨባጭ ሊጠና የሚችል ነው ወይሰ
አይደለም?
ጥናት ሊካሄድበት የታሰበበት ችግር ወይም ሁኔታ ምን ያህል ተፈላጊ ነው? ማለትም ጥናቱ ምን ችግርን
ለመፍታት ይጠቅማል? የሚለው በጣም ቁልፍ ጥያቄ ነው፡፡ ምክንያቱም የጥናት አንድ ዋና አላማ ለጥናቱ ብቻ
ሳይሆን የሚደረገው ጥናት አንድ ችግር ወይም እንቆቅልሽ የሚፈታ ሊሆን ይገበዋል፡፡
ጥናት ሊካሄድበት የታሰበበት ችግር ላይ አጥኚው ምን ያህል ለማወቅ ፍላጎት አለው? ምክንያቱም አጥኚው
በሚያደርገው ጥናት ላይ ፍላጎት ከሌለው ጥናቱ የሚጠይቀውን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ሊሆን
አይችልም፡፡ ጥናት ብዙ መስዋዕትነት የሚጠይቅ ነው፡፡በተለይ የጊዜ፤ የትግስት እነዲሁም ሌሎች፤
ጥናት ሊካሄድበት የታሰበበት ጉዳይን በሚመለከት አጥኚው ጥናቱን ለማካሄድ ተፈላጊውን በቂ እውቀት እዳለው
ከመጀመሪያ እርግጠኛ መሆን ይገባዋል፤
ከዚህ በተጨማሪ ጥናት ሊካሄድበት የታሰበበት ጉዳይ ወይም ችግር ላይ መረጃ ለመሰብሰብ የሚያስችል ሁኔታ
መኖሩንና እንዲሁም ለጥናቱ የሚያስፈልጉት መሳሪያወች እንደሚገኙ ማረጋገጥ፤
ጥናቱ ሊካሄድት በታሰበበት ችግር ወይም ሁኔታ ላይ ጥናት እንዲካሄድበት በሃሳብና በገንዘብ የሚደግፍ
ድርጅት መኖሩን ማወቅ ይበጃል፤
1 Page 10 of 47
ከዚህም በላይ ጥናቱን ለማካሄድ የሚያስፈልገውን ገንዘብ፤ የቁሳቁስ፤ የሰው ሃይልና ጊዜ ምን ያህል
መሆኑን መተመን ያስፈልጋል፤
በመጨረሻም ጥናቱ ሊያስከትል የሚችለው ውጣ ውረድ፤ አደጋ እና መሰናክል ከመጀመሪያው መገመትና መዘጋጀት
ተገቢ ይሆናል፡፡
2.2.3 ከጥናቱ ግኝቶች አጠቃላይ ግንዛቤ መውሰድ (internalization)
በአንድ ርዕስ ላይ ጥናት የሚካሄደው በርዕሱ ላይ ጥናት ከተካሄደ በኃላ የተከሰቱት ግኝቶች በርዕሱ ላይ አጠቃላይ
ግንዛቤ ለመውሰድ እንዲያስችል ነው፡፡ እንደሚታወቀው ጥናት የሚካሄደው ለናሙና በተመረጡ መላሾች ሲሆን እነዚህም
ለናሙና የተመረጡ መላሾች ሁሉን ይወክላሉ ተብሎ ታምኖበት ቢሆንም የተገኘውም የጥናት ውጤት ሁሉን አስከምን ድረስ
እንደሚመለከት አጠቃላይ ግንዛቤ ከጥናቱ የስፋትና ጥልቀት ወሰን የዘለለ መሆን የለበትም፡፡
በተጨማሪም አጠቃላይ ግንዛቤው በጥናቱ የተሰበሰበው መረጃ ከሚደግፈው ውጭ እንዳይሆን መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡
በጥናቱ ስለተገኙት ግኝቶች አጠቃላይ ግንዛቤ ሲሰጥ የሚከተሉትን ነጥቦች ማጤን ይገባዋል፡፡
ስለ ግኝቶች የሚሰጠው አጠቃላይ ግንዛቤ በጥናቱ አላማና በሚገኘው መረጃ ላይ ብቻ መሆን አለበት
እንጂ ከዚህ ውጭ መሆን የለበትም፤
ስለ ግኝቶች የሚሰጠው አጠቃላይ ግንዛቤ በጠንካራ ማስረጃ ላይ የተመሰረተ እንጂ በትንሽ ፍንጭ ላይ
የተመሰረተ መሆን አይገባውም፤
በጥናቱ ውስጥ ባልነበሩ አዲስ መረጃ ላይ የተመሰረተ አጠቃላይ ግንዛቤ ማቅረብ ተገቢ አይደለም፤
በስህተት ላይ የተመሰረተ ትንታኔና አተረጓጎም እንዳይኖር ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል፤
እንዲሁም አጠቃላይ ግንዛቤው የአጥኚውን የግል አስተሳሰብ ወይም የተሳሳተ አስተሳሰብ
የሚያንፀባርቅ መሆን አይገባውም፡፡
መላምት፡-
የአንድ ጥናት መሰረታዊ ጥያቄ ጊዜያዊ መልስ የሚሰጥ ፤ አንድ አጥኚ ጥናት ሊያደርግ ሲነሳ በአእምሮ ውስጥ
ለሚመላለሱ ጥያቄዎች ወይም “እንዲህ ይሆን?” ለሚለው ጥርጣሬ የሚሰጠው ጊዛዊ ምላሽ ፤ በጥናት ተግባራዊ ሂደት ውስጥ
የሚፈተሽና የሚረጋገጥ ሲሆን ይህም
1 Page 11 of 47
ያስፈለገበት ምክንያት ለጥናት ተግባር ሂደት የተፈተሸና የተረጋገጠ እውነታ በማፍለቅ የሰዎችን የእውቀት አድማስ
በማስፋትና በማጠናከር የጥናቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ነው፡፡ መላምት ከንድፍ ሃሳብ፤ ከምልከታ ወይም ከእነዚህ ከሁለቱም
በጋራ ጥምረት ሊፈልቅ ይችላል፡፡
መላምቱ ግልፅ ሁኖ መስፈር አለበት፤ በጥናት ተግባራዊ ሂደት ውስጥ መላምቱን ለመፈተሽና ለማረጋገጥ
አንዲቻል በመላምቱ ውስጥ ሊጠቃለሉ የሚችሉትን ተለዋዋጭ ሁኔታዎች በግልፅ ማስቀመጥ አስፈላጊ ነው፡፡
መላምት በፍተሻ ሊረጋገጥና ሊጣራ የሚችል ሁኖ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ የአንድን መላምት ተጨባጭ መረጃዎች
አሰባስበን በሚደረገው ትንታኔ ትክክለኛነቱን ለመፈተሽ ወይም ለማረጋገጥ ይቻላል፡፡ መላምቱን መሰረት
ያደረገ መረጃ መሰብሰብና የመተንተን ሂደት ተግባራዊ ማድረግ ላይ ችግር ከገጠመን ግን መላምቱ ሊፈተሽ ወይም
ሊረጋገጥ የማይችል ነው፡፡ ይህን አይነቱን መላምት መተው ያስፈልጋል፡፡
መላምቱ የተንዛዛ ሆኖ መቅረብ የለበትም ከመላምቱ ጋር አብረው ተያይዘው ሊታዮ የሚገባቸው በጥናቱ ውስጥ
መረጃ በማሰባሰብ፤ ልንመልሳቸው ያቀድናቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች ናቸው፡፡ በጥናቱ ወይም በምርምሩ ሂደት
ውስጥ የሚመለሱት እነዚህ መሰረታዊ ጥያቄዎች አስቀድመን ያሰፈርነውን መላምት እውነት መሆን ወይም አለመሆን
የሚያረጋግጡ መሆን አለባቸው፡፡
የጥናት ርዕሶችን በመፈለግ፤ በመምረጥ፤ ለይቶ በማስቀመጥ ሂደት አስፈላጊ ጥንቃቄዎች መደረግ ይኖርባቸዋል፡፡
ይኸውም፡-
I. የምርምር ርዕስ ሲመረጥ በቅድሚያ በጉዳዮ በቂ እውቀትና ስለጉዳዩም አወንታዊ ፍላጎት ስለመኖሩ መረጋገጥ
አለበት፤ ከአጥኚው ልምድ፤ እውቀትና ፍላጎት ውጭ እንዳይሆን፡፡
II. ርዕሰ ጉዳዩን በሚመለከት ጥናቶች ተሰርተው ከሆነ የተለየ ነገር እናሳያለን ብለን ካመን በጉዳዮ ልንገፋ
እንችላለን፡፡
III. መረጃዎች እየተጠናቀሩ በራሳቸው ተፋሰስ እንዲሄዱ የሚያስችል ርዕስ መምረጥ
IV. የጥናት ርዕስ ስንመርጥ ከስሜታዊነት ነፃ ሆነን በነፃ አዕምሮ ልንሰራው የምንችለውን መምረጥ፤
V. የጥናት ርዕስ ስንመርጥ ጥናታችን ሊመልሰው የሚገባ ጥያቄ ወይም ሊፈታ የሚገባ ችግር መኖሩን ማረጋገጥ
አለብን፡፡
VI.
1 Page 12 of 47
ከዚህ በተጨማሪ አንድ አጥኚ የጥናት ርዕሱን ለመግለፅ በሚሞክርበት ጊዜ አስቀድሞ የነደፈውን መላምትና መሰረታዊ
ጥያቄ በአእምሮው መያዝ ይኖርበታል፡፡ይህንን ዘንግቶ የጥናት ርዕስ ላይ መሰማራት የሚፈለገውን ውጤት እንዳይገኝ
እንቅፋት ሊሆነ ይችላል፡፡
ምእራፍ 3
3. የናሙና አወሳሰድ ዘዴዎች (sampling techniques)
መረጃ በሚሰበሰብበት ወቅት ጥናቱ የሚመለከታቸውን ማንኛውንም ሰው ወይም ነገር ሁሉ ለመረጃ ሰጭነት መጠቀም ብዙውን
ጊዜ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ ይህ አይነቱ አሰራር የማያመችና አንዳንዴም የማይቻል ከመሆኑም በላይ ብዙ ገንዘብ፤ ጊዜና
ጉልበት ይጠይቃል፡፡ አማራጩ ከጠቅላላው ጥናቱ ከሚመለከታቸው ሰዎች መካከል ጥቂቶቹን መርጦ ለጥናቱ የሚያስፈልገውን
መረጃ ከነሱ መሰብሰብ ነው፤ ይህም ናሙና ይባላል፡፡
በዚህ መልክ የሚወሰደው ናሙና ጥናቱ የሚመለከታቸውን ሰዎች ወይም ነግሮች ሁሉ የሚወክል መሆን ይኖርበታል፡፡ ናሙናው
ወካይ ከሆነ የጥናቱ ውጤት መረጃው ከሁሉም ሰዎች ወይም ነገሮች ተሰብስቦ ትንተናው ቢካሄድ ኑሮ ከሚገኘው ውጤት ወይም
መንደርደሪያ ጋር ተመሳሳይ ይሆናል፡፡
ጥናቱ ለሚመለከተው ለዕያንዳዱ አባል በናሙናነት የመወሰድ እድል ያለው መሆኑን አለማረጋገጡ ነው፡፡
1 Page 13 of 47
እኩል እድል ከማይሰጡ የናሙና አይነቶች ዉስጥ የሚከተሉትን በምሳሌነት መመልከት ይቻላል፡-
በተለያየ መልኩ ሊከናወን ይችላል፡፡ የዚህ ዘዴ ዋና ባህሪ ደግሞ ለእያንዳዱ አባል በናሙናነት የመወሰድ
ተመሳሳይ እድል መሰጠቱ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ በዚህ ዘዴ የሚወሰድ ናሙና ጥናቱ የሚመለከታቸውን ሁሉ የመወከል
ሃይሉ እኩል እድል ከማይስጥ ናሙና በጣም የተሻለ ነው፡፡
1 Page 14 of 47
የተመጣጠነ ቁጥር የያዘ መሆን ስላለበት የምድብ እጣ ናሙና ዘዴ ለመጠቀም እንገደዳለን ማለት ነው፡፡
ቡድን/ክልል/ ናሙና(Area sampling) በናሙናነት የሚመረጡት ግለሰቦች/ነገሮች/ ሰፋ ባለ ቦታ
የሚመረጡ ተበታትነው የሚገኙና በጣም ብዙ ሲሆን ከአንድ የእጣ ናሙና አወሳሰድ ዘዴ ለመጠቀም አስቸጋሪ
ስለሚሆን ጥናቱ የሚመለከታቸው ሰዎች በቡድን ናሙና መጠቀሙ ጊዜ፤ ጉልበትና ገንዘብ ከመቆጠብ ባሻገር
የበለጠ ምቹ ይሆናል፡፡
ምእራፍ 4
ጥናት ለማካሄደድ አስተማማኝ መረጃዎችን ማሰባሰብ አስፈላጊ ነው፡፡ በተለይ የጥናቱ ዋና አላማ አሁን በጊዜው
በተጨባጭ የተከሰተ ሁኔታን ወይም ችግርን ለማጥናት ከሆነ መረጃው ወቅታዊ ቢሆን ይመረጣል፡፡ ምክንያቱም ጊዜ
ያለፈበት መረጃ ከሆነ ያሁኑን ሁኔታ ወይም ችግር ለማጥናት አይጠቅምም፡፡
1 Page 15 of 47
መጠይቅ ከመውጣቱ በፊት ጥናት ስለሚደረግበት ርዕስ ብዙ ማወቅ ማለትም በርዕሱ ላይ ቀደም ብለው የተፃፉ ፅኁፎችን
ማንበብ እንዲሁም የጥናቱን አላማ መወሰን ለምንስ አይነት ጥያቄዎችና መፍተሄዎች ምላሽ እንዲያስገኝ እንደሚፈልግ
አጥኚው መወሰን ይገበዋል፡፡ መጠይቅ ለማውጣት ሲታሰብ የአጠያየቁን ዓይነት መወሰን ያስፈልጋል፡፡
ሀ/ ነፃ ምላሽ የሚያሰጡ፡ ጥያቄው ክፍት ሆኖ መላሹም እንደልቡ ሃሳቡን የሚሰጥበት ነው፡፡ መላሹ በአመላለሱ
አይገታም፤ አጥኚውም ያላሰበውን አንዳንድ አዳዲስ ሃሳቦች ከመላሾች እንዲያገኝ ያስችላል፡፡
ለ/ዝግ የሆነ ምላሽ የሚያሰጥ፡ ዓይነቱ አጠያየቅ የሚያስገኘው መልስ ውስን ነው፡፡
1 Page 16 of 47
በመጠይቁ መስፈር ያለባቸው
በመጠይቁ መጀመሪያ ላይ አጥኘው የስራ ቦታ፤ አድራሻና እንዲሁም የጥናቱ አላማ ምን እንደሆነ በግልፅ መፃፍ
አለበት፤
መላሾች መጠይቁን ሲሞሉ ስማቸው መፃፍ የማይገባቸው መሆኑን መጠቀስ አለበት፤
የመጠይቁ አስፈላጊነት (የጥናቱ ዋና አላማ) በግልፅ መጠይቁ እንዴት መሞላት እንደሚገባው በመጠይቁ መጀመሪያ
ላይ ግልፅ እና አጠር ያለ መመሪያ መስጠት ያስፈልጋል፤
መጠይቁን እንዲሞሉ የተጠየቁ ሰዎች በጎ ፈቃድና የጥናትን ጥቅም በመገንዘብ እንጅ በግዴታ ስላልሆነ
ለሚያሳዮት በጎ ፍቃድና ትብብር እንዲሁም መጠይቁን ለመሙላት ለሚያጠፉት ጊዜ ማመስገን ተቢ መሆኑን አጠር
ያለ ምስጋና በቃለ-መጠይቁ ላይ ቢታከልበት አይከፋም፤
ጠያቂና መላሽ ግንባር ለግንባር በመገናኘት መረጃ የሚሰበስቡበት ስልት ነው፡፡ በተለይም ማንበብና መፃፍ
ከማይችሉና ከህፃናት መረጃ ለመሰብሰብ ይጠቅማል፡፡ ቃለ-መጠይቅን ልክ እንደ ፅሁፍ መጠይቅ በጥንቃቄ ማዘጋጀት
ያስፈልጋል፡፡ ቃለ መጠይቅ በሚገባ ከተዘጋጀ በኃላ የሚከተሉትን ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡
1 Page 17 of 47
መላሹ ከተወሰነው ጊዜ በላይ መልስ መስጠቱን ለመቀበል ከፈለገ የቃለ መጠይቁን ጊዜ ማራዘም ይቻላል፡፡
ምቹ ቦታና ጊዜ መምረጥ ያስፈልጋል፤
4.2. የጥናቱ ፅሁፍ ሲዘጋጅ መካተት የሚገባቸው
I. የጥናቱ ርዕስ(Topic)
በርዕስ ገፅ ላይ የሚኖሩ ቃላት በጥንቃቄ መመረጥና ቃላቱም የተመጠኑ እና ጥናቱን በደንብ የሚገልፁ መሆን
ይኖርባቸዋል፡፡
በርእስ ገፅ ላይ መካተት የሚገባቸው ነገሮች፡-
የጥናቱ ርዕስ
የአጥኝዎቹ ሰምና አድራሻ
ጥናቱ የሚቀርብለት ድርጅት
የጥናቱ ፕሮፖዛል የሚቀርብበት ቀንና አመት
II. ምስጋና(Acknolodgement)
ጥናቱ ሲካሄድ ለአጥነው በገንዘብ፤ በማማከር፤ አጥኒውን በማበረታታት እና የተለያዮ ድጋፍ በማድረግ ጥናቱ
እንዲሳካ ለተባበሩ ሁሉ ስማቸውን በመግለፅ ምስጋና የሚገለፅበት ክፍል ነው፡፡
ማውጫ አንባቢዎች ማንበብ የሚፈልጉትን ክፍል በቀላሉ እንዲያገኝት የሚረዳ ነው፡፡ማውጫ ሁሉንም ርዕሶችና
ንዕስ ርዕሶች እስከሚኙበት ገፅ ጭምር ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡
ጥናቱ በሚካሄድበት ርዕስ ላይ የሚያጋጥሙት ሙያ ነክ ቃላትን ወይም ሀረጎችን በጥናቱ ውስጥ እንደተሰጣቸው አተረጓጎም
ወይም አነባበብ መግለፅ ይኖርባቸዋል፡፡በተጨማሪም ምህፃረ ቃሎችን ከተጠቀምን ምህፃረ ቃሎቹንና ትርጉማቸውን
ማስቀመጥ ያስፈልጋል፡፡
VI. መግቢያ(Introduction)
መግቢያ ለአንባቢዎች የጥናቱን መነሻ መረጃ የሚሰጥ ነው፡፡ የመግቢያ ፅሁፍ ስፋት እንደ ጥናቱ
ቢወሰንም ከአንድ ገፅ በላይ መብለጥ ለበትም፡፡
መግቢያ፡-
1 Page 18 of 47
በዚህ ርዕስ ውስጥ ጥናቱ የሚያስፈልግበትን ምክንያትና ጥናቱ ለድርጅቱ የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ገላጭ በሆነ
መልኩ መቀመጥ አለበት፡፡
በአንድ ርዕስ ላይ ጥናት የሚካሄደው አስፈላጊነት ሲኖረው እንጂ እንደዚሁ ለጥናትነቱ ብቻ አይደለም፡፡ ስለዚህ
አንድ ጥናት ሲካሄድ ለአስፈላጊነቱ የሚከተሉትን ማየት ይገባል፡፡
ሀ.ጥናቱ ሊካሄድበት የታሰበው ርዕስ ጥናት ቢካሄድበት ስለችግሩ ወይም ሁኔታው የበለጠ ማወቅ ስለሚያስችል፡
ለ. በጥናት ርዕሱ ላይ ጥናት ቢካሄድ ለችግሩ መፍተሄ ለማግኘት ስለሚረዳ፤
ሐ.በጥናት ርዕሱ ላይ ጥናት ቢካሄድበት ሌሎች አጥኒዎች ወደፊት ይህን ፈለግ በመከተል በርዕሱ ላይ በስፋትና
በጥልቀት ጥናት እንዲያደርጉ ሊያበረታታ ስለሚችል፤
መ.በዚህ ርዕስ ላይ ጥናት ቢካሄድ እስካሁን የነበረውን የእውቀት አድማስ ለማስፋት ስለሚያስችል፡፡
ስለዚህ አንድ የጥናት ርዕስ ከላይ ከተጠቀሱት ምክንያቶች መካከል በሁሉም እንኳን ባይሆን በጥቂቱ የተነሳዉ
አስፈላጊነት ወይም ጥቅም እንዳለው መግለፅ ተገቢ ይሆናል፡፡
IX. የጥናቱን ወሰን ማመላከት(Scope of the study):-
የጥናቱ ወሰን ሲባል ጥናት የሚካሄድበት ርዕሰ ጉዳይ ስፋቱና ጥልቀቱ እስከ ምን ያህል እንደሚሆንና የጊዜውን ሁኔታ
በግልፅ መለየት ማለት ነው፡፡
1 Page 19 of 47
በጥናቱ ምን ምን እንደሚሰራ
የጥናቱ ዳራ እስከምን ድረስ እንደሆነ እና ጥናቱ የሚጠናቀቅበትን ጊዜ ማመላከት ይኖርበታል፡፡
X. ጥናቱን ለማካሄድ ታሳቢ ችግሮች(Limitation)
አንድ ጥናት እንደተፈለገው በሚገባ ለማካሄድ ብዙውን ጊዜ አይቻልም፡፡ ምክንያቱም ለጥናቱ አስፈላጊ ሆነው
የሚገኙ ነገሮች ሁሉ ሙሉ በሙሉ ላይሟሉ ስለሚችሉ ነው፡፡ አንዳንዶቹ ከቁጥጥር ውጭ በመሆናቸው ሌሎች ደግሞ ሊገኙ
ባለመቻላቸው ይሆናሉ፡፡ ስለሆነም አጥኚው እነዚህን ነገሮች ለይቶ በማወቅ ጥናትን እንደተፈለገውና በሚገባ
ለማካሄድ ችግር ፈጥረውበት እንደሆነ መግለፅ ያስፈልጋል፡፡
XI. የጥናቱ ዘዴና አካሄድ(Methodology of the study):-
እንደ ርዕሱ ጠባይና እንደዚሁም እንደጥናቱ አላማ የጥናቱ ዘዴ የተለያየ ሊሆን ይችላል፡፡ ለምሳሌ ገላጭ ጥናት
(Descriptive research) ፤ የፕሮጀክት ጥናት (project Research)፤ ታሪካዊ(Historical
Research) ጥናት ወይም በሙከራ የታገዘ ጥናት(Experimental research) ሊሆን ይችላል፡፡
ከዚህ በኃላ መረጃ ለመሰብሰብ ሊጠቀሙበት የታሰበውን የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ መጠቆም አለበት፡፡ የመረጃውም
መሰብሰቢያ ዘዴ እንዴት አንደተዘጋጀ፤ ምን አይነት ሙከራ እንደተካሄደበት፤ እንዴት እንደተሰራጨ እና
እንደተሰበሰበ መጥቀስ ያስፈልጋል፡፡ በሙከራ የታገዘ ጥናት (Experimental Research) ከሆነ ምን
አይነት የላብራቶሪ ወይም መስክ ሙከራ እንደተካሄደ ለምን ያህል ጊዜና በምን አይነት አኳኋን እነደተካሄደ
በዝርዝር መግለጽ ይኖርበታል፡፡
በተጨማሪም ለጥናቱ ምን የናሙና አይነት እንደተመረጠ ለምንስ እንደተመረጠ መግለፅ ይኖርበታል፡፡ የናሙናውም
ይዘትና አመራረጡም እንዴት እንደሆነና ለምንስ እንደዛ እንደሆነ ማብራራት ተገቢ ይሆናል፡፡
1 Page 20 of 47
እንዲሁም የተሰበሰበው መረጃ በምን አይነት ስታትስቲካዊ ስልት እንደሚተነተንና ለምንስ በምን አይነት ስልት
እንደሚተነተን፤ በተጨማሪም የተመረጠውን ስልት አስተማማኝነት መገለፅ ያስፈልገዋል፡፡
የተገኙ የጥናት ውጤቶች በአብዛኛው በሰንጠረዥ በተደገፈ ትንተና መቅረብ ይገባቸዋል፡፡ እያንዳዱ ሠንጠረዥ ርዕስ
ሊኖረው ይገባል፡፡ በሠንጠረዡም ውስጥ የሚቀርቡት ግኝቶች በአኃዝ ከመቅረባቸውም በላይ ለአንባቢ ግልጽ በሆነ ሁኔታ
መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጥናት ውጤቶች የሚቀርብበት በሠንጠረዥ ብቻ ሳይሆን በተለይ የዋና ግኝቶች መተንተንና
መተረጎምም በጣም ተገቢ ይሆናል፡፡ አንድን ጥናት ጥናት የሚያሰኘው አጥኚው የሳይንስና የሎጂክን ስልት በመከተል
በግኝቶቹ ላይ የሚደረገው ትንታኔና ትርጉም እንጂ ጥሩ የሆኑ መረጃ በማቅረብ ብቻ አይደለም፡፡
1 Page 21 of 47
የአንድን ጥናት ደረጃ ከፍተኛነቱ ወይም ዝቅተኛነቱ የሚለካው በዚሁ ነው፡፡ስለሆነም የምርምርን ግኝቶች በጥንቃቄ
ለመተንተንና ለመተርጎም የሚከተሉትን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
XIV.ማጠቃለያ(Conclusion)
እንደሚታወቀው አንድ የጥናት ሥራ እንደሁኔታው ስፋትና ጥልቀት አለው ስለሆነም ጥናቱን ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው
አንብቦ ለመረዳት ጊዜ የሚጠይቅ ጉዳይ ይሆናል፡፡ ብዙ አንባቢያን ባላቸዉ ጥቂት ጊዜ ውስጥ የጥናቱን ፍሬ ነገር
በቀላሉ እንዲረዱት አሳጥሮ ማቅረብ አስፈላጊ ነው፡፡ በተቻለ መጠን የጥናቱን አላማ ባጭሩ ማስቀመጥ እንዲሁም
አበይት የሆኑትን ግኝቶች ባጭሩ ማስፈር ተገቢ ይሆናል፡፡በዚህ ርዕስ የሚቀመጠዉ ማጠቃለያ ሀሳብ አሁንን የሚገልፅ
መሆን አለበት፡፡
የመፍተሄ ሃሳቦች ሊመነጩ የሚችሉት በመጀመሪያ ደረጃ የችግሩ መንሰኤዎች በጥናት በውል ከታወቁ በኃላ
ነው፡፡የመፍተሄ ሀሳቦች በመጀመሪያ ሊቀርቡ የሚችሉት የችግሩን መንሰዔዎች በጥናት ከተረዳው
ከተመራማሪው ሊሆን ይችላል፡፡ ሆኖም ግን አጥኚዉ በመጠይቁ ውስጥ ምላሾቹን ስለችግሩ የመፍተሄ ሀሳብ
እንዲሰጡ በማድረግ
LOGO Form No.:
ኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበር OP/KTSC/044
KOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY
ማንዋል . Page No.:
Issue No
1 Page 22 of 47
ከተጠቆሙት የመፍተሄ ሃሳቦች ሊጠቅሙ የሚችሉትን በመምረጥ በመፍትሄ ሃሳቦቹ ውሰጥ ሊያካትታቸው
ይችላል፡፡
የመፍተሄ ሃሳቦች በሚሰጡበት ጊዜ ግንዛቤ የሚያስፈልገዉ የሚሰነዘሩት የሚፈትሄ ሃሳቦች ባለው ተጨባጭ
ሁኔታ ተግባራዊ ሊሆን የሚችሉ መሆናቸውን ነው፡፡ ምክንያቱም በተግባር ሊተረጎሙ የማይችሉ የመፍተሄ
ሃሳቦች ማቅረብ ዋጋ የለውም፡፡
XVI. አባሪ(Appendices):-
ጥናቱ ለማካሄድ የተጠቀምናቸውን መረጃዎች ማለትም መጠይይቆች፤ የተለያዮ ፕሮግራሞች እና ሌሎች ፎርማቶች ከጥናቱ
ጋር ተያይዘው የሚቀርቡበት ነው፡፡
XVII. ማጣቀሻ(Reference)
በዚህ ክፍል የጥናቱ እውነተኛነት ይመለከትበታል፤ የተቀምናቸው የመረጃ ምንጫቸው በማን እንደተፃፈ፤ መቼ
እንደፃፈ የመረጃ መረቡ ስም በግልፅ መቀመጥ አለበት፡፡
1 Page 24 of 47
ምእራፍ 1
1.1 ትርጉም
ፕሮጅክት ውስን የሆነ ውስን በሆነ ጊዜና ቦታኢንቨስት በማድረግ አንድ አላማን የምታስፈፅምበት ድርጊት ነው፡፡
በሀብት አጠቃቀም/ በጀት/ ደረጃም በውስን ተመድቦለት የሚፈፀም ተግባር ነው፡፡ በሌላ መንገድ ፕሮግራም የተለያዮ
ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ የተቀመረ ሰፊ የፕሮጀክቶች ስብስብ ነው፡፡ በጊዜ፤ በበጀትና በውጤት ደረጃም በጣም ሰፊ
የሚሆን ነው፡፡
በፅንሰ ሃሳብ ደረጃ ሳይንሳዊ የሆነ ዐቅድ አሰራር የሃብት ብክነትና ጉድለት በማስቀረት ቀልጣፋና ውጤታማ በሆነ
መንገድ የተቀመጡ ግቦችንና ዓላማዎችን ከዳር ለማድረስ የሚያስችል ሂደት ነው፡፡
ፕሮጀክት ማለት ወደፊት ጥቅም ያስገኛል ብሎ በማሰብ የተወሰነ ሃብትን ስራ ላይ በማዋል ማንኛውም የኢንቨስትመንት
እቅድ ነው፡፡ ዓላማውም ውስን ሆነውን እምቅ ሃብት ይበልጥ ጠቀሜታ ሊያገኝ የሚችል የልማት እንቅስቃሴ ላይ በማዋል
ከወጪው የበለጠ ወይም እኩል የሆነ ጥቅም ማስገኘት ነው፡፡
ለዕድገትና ውጤታማነት
ውጤታማነት፤ በጥራት፤ በብዛት፤ ተደራሽነት እና ድንገተኛ ችግሮችን ለመቀነስ
ሃብትን በቁጥባ ለመጠቀም፤ ጊዜን በአግባቡ ለመጠቀም፤ ወጪን ለመቀነስና የሰው ሀይልን መጥኖ
ለመጠቀም ይረዳል፡፡
የአገልግሎት ስርጭትን በእኩል ለማዳረስ
የአደጋ ተጋላጭነትን ለመቀነስ
ምዕራፍ ሁለት
በፕሮጀክት ዑደት ተተንትነው ያለፉ ፕሮጀክቶች በተግባር ተፈፃሚ የመሆን እድላችው ከፍተኛ ከመሆኑ በላይ
የታለመላቸውን ዓላማ በመምታት ለዕድገት የጎላ አስተዋፅኦ አላቸው፡፡
1 Page 25 of 47
አንድ ድርጅት በፕሮጀክት ልየታ ወቅት የመጀመሪያ ስራው ፕሮጀክት የሚሰራበትን የድርጅቱን ዋነኛ ችግር ማወቅ
ይሆናል፡፡ ይህን ችግር ያገባኛል ባዮች/stakeholders/ያካተተ ስለድርጅቱ ዋነኛ ችግር የሃሳብ ማሰባሰቢያ
የውይይት መድረክ ሊያዘጋጅ ይገባል፡፡ በውይይቱ ወቅት የሚቀርቡት ችግሮች ብዙ ሊሆኑ ቢችሉም የችግሮችን ስፋትና
ጥልቀት በመረዳት በደረጃ አስቀምጦ ዋነኛ ችግሩን/core problem/መለየት ይጠይቃል፡፡ ከዚህ ለመድረስ የችግሩን
ዘርፈ ብዙ ቅርንጫፍ/problem tree/ ማስቀመጥ መተንተን ያስፈልጋል፡፡የችግሩ መኖር ያስከተለው
ተፅዕኖ/Impact or effect/ በዝርዝር ማውጣትና ለዚህ ችግር መንሰኤ የሆኑ ምክንያቶችን /cause/ መለየት
ይኖርባቸዋል፡፡ የዚህ ችግር ተፅዕኖ ከምክንያቶቹ ጋር ያለው ግንኙነትና ተያያዥነት በመተንተን ማስረዳት
ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ ትንተና በመነሳት የፕሮጀክቱን ግብና ዓላማ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ችግሩ በድርጅቱ ለምን
እንደተፈጠረ፤ መቸ እንደተፈጠረ፤ በየትኛው የድርጅቱ ክፍል ላይ ችግሩ እንደሚያጠነጥን ማሳየትና ችግሩ ያስከተለውን
ውጤት ማወቅ ተገቢ
1 Page 26 of 47
ይሆናል፡፡ የዚህን ችግር ዋነኛነትን አጉልተው የሚያሳዮ ሌሎች አሀዛዊ መረጃዎችን በማሰባሰብ ትክክለኛነቱን
ማስረገጥ ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ አንድን ችግር ስናጠና የማን፤ ምን አይነት፤ የት፤ ለምንና መቸ የሚሉ ጥያቄዎችን
የሚመልስና በዝርዝር የሚያስረዳ መሆን ይኖርበታል፡፡
ግብ ሰፊ የሆነና አንድና ከአንድ በላይ የሆኑ ፕሮጀክቶች በመጨረሻ ሊደርሱ የታሰበበት በለውጥ ሂደት የሚመጣ ውጤት
ነው፡፡ ዓላማ ከአስቀመጥነው ግብ የሚመነጭ በመጠን፤ በጥራት፤ በወጭና በጊዜ የሚለካ ከግብ የጠበበ የፕሮጀክቱን
ችግር ለማቃለል የሚችል የአጭር ጊዜ ውጥን ነው፡፡
የፕሮጀክት ዝግጅት ከ 7-10% የፕሮጀክት አጠቃላይ ዋጋ ያወጣል ተብሎ ስለሚገመት በጥንቃቄ መስራት ያስፈልጋል፡፡
ስለሆነም በፕሮጀክት ዝግጅት ወቅት የቅድመ ዝርዝር ጥናትና የዝርዝር ጥናት እንደአስፈላጊነቱ ማየትና ማጥናት ተገቢ
ነው፡፡
ይህ ጥናት በቅድሚያ ከፍተኛ ወጭ በማውጣት ዝርዝር ጥናት አጥንቶ የማያዋጣ መሆኑን ከማረጋገጥ በአነስተኛ ወጭ
የመጀመሪያ ጥናት በማካሄድ የፕሮጀክቱን ተስፋ ሰጭነት ለማረጋገጥ ይረዳል፡፡
በቅድመ ዝርዝር ጥናትና በዝርዝር ጥናት መካከል የሚካሄደው የጥናት ሂደት ተመሳሳይነት ያለው ሲሆን ልዮነቱ
የሚከሰተው በትንተናው የስፋት ደረጃና በሚሰበሰበው መረጃ ብዛትና ጥራት ነው፡፡ በዚህ ጥናት እንደሌሎቹ ጥናቶች
ፕሮጀክቱ ተቀባይነት እንዲኖረው ወይም ውድቅ እንዲሆን ለመወሰን የሚያስችለውን ሃሳብ ለማግኘት እንዲቻል እስከ
መጨረሻው ጥቃቅን ጉዳዮች ድረስ በዝርዝር የሚታይበት የፕሮጀክት ዑደት አካል ነው፡፡ በደንብ የተዘጋጀ የፊዚቢሊቲ
ጥናት በመጀመሪያ የፕሮጀክት ጥናት የታዮ ጉዳዮችን ሁሉ በመመርመር እንደገና በትክክለኛው መንገድ ያስተካክላል፡፡
የፕሮጀክቱ ግብና ዓላማ በትክክል ከፕሮጀክቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው መሆኑን ያረጋግጣል፡፡
1 Page 27 of 47
ፕሮጀክቱ ተፈፃሚ በሚሆንበት ወቅት ሊያስከትላቸው የሚችሉ ችግሮች ወይም አመቺ ሁኔታዎች በዚህ ውስጥ ይተነተናሉ፡፡
ለችግሮቹም መፍተሄ ሊሆኑ የሚችሉ አማራጮች ይቀመጣሉ ስለፕሮጀክት ስናስብ ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ያለብን ሁሉም
ፕሮጀክቶች አንድ አይነት የጥናት ወይም የአሰራር ዘዴ አይኖራቸውም፡፡ ስለሆነም በአንዱ ፕሮጀክት ላይ ሁሉም ነገር
በዝርዝር ሲታይ በሌላው አላስፈላጊ ሆኖ የሚታለፍ የጥናት ዓይነት ሊኖር ይችላል፡፡
በዚህ ስር የሚተነተኑት የገበያ ጥናት ማካሄድ፤የፕሮጀክት ቴክኒካዊ ሃሳቦች ማጎልበት፤ ስለ ፕሮጀክቱ አመራርና
ድርጅታዊ መዋቅር ሃሳብ ማቅረብ፤ ስለ አካባቢው ተፅዕኖ ማጥናት፤ ስለ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሁኔታ ማጥናት፤ እንዲሁም
የፕሮጀክቱን ወጪና የሚያስከኘውን ጥቅም መተንተን ይሆናል፡፡
የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ ፕሮጀክቱ ለድርጅቱና ለአካባቢዉ ለያስገኝ የሚችለዉን ጥቅምና የሚያስከትለዉን ተፅእኖ
ለይቶ ማስቀመጥ ይሆናል፡፡ ፕሮጀክቱን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚመለከቱ ሁኔታዎች በሙሉ ማለትም ኢኮኖሚያዊ፤
ማህበራዊ፤ አስተዳደራዊ ፖለቲካዊና ጂኦግራፊያዊ ሁኔታዎችን መዳሰስ ያስፈልጋል፡፡
የፕሮጀክቱ ምርት በሚቀርብበት የገበያ ሁኔታ በቀጠና እና ተጠቃሚ ተለይቶ መጠናት ይኖርበታል፡፡ ለፕሮጀክቱ ምርት
በቂ ገበያ በሃገር ውስጥ ወይመ በውጭ አገር መኖሩ ወይም አለመኖሩ መረጋገጥና ምርት የሃገር ውስጥ ገበያን ፍላጎት
በምን ያህል እንደሚያረካ መገምገም ያስፈልጋል፡፡ አስካሁን ድረስ ድርጅቱ ተመሳሳይ ምርቶችን ከየት ሲያገኝ
እንደነበር መብራራት ይኖርበታል፡፡ለምርት የተተመነው ዋጋ አሁን በገበያ ላይ ከሚሸጠው ወይም ከሚቀርቡት
ተመሳሳይ ምርቶች ጋር እንደሚነፃፀር መግለፅ ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም የተለያዮ አመታት የፍጆታ መረጃዎችን
/consumption coeficcient/ በመጠቀም፤ ጥቅም ላይ የዋሉ የምርትና የግብዓት መረጃዎችን /input-out
put model/ መጠቀም በወቅቱ አመች የሆነውን ዘዴ በመምረጥ ሳይንሳዊ የሆነውን መንገድ ተንትኖ የገበያውን
አጠቃላይ ሁኔታ መረዳት ያስፈልጋል፡፡
ይህን የትንበያ ጥናት ማካሄድ በፕሮጀክቱ አገልግሎት እድሜ ውስት ሊገኝ የሚችለውን የገበያ አዋጭነት ለማጤን
ይረዳል፡፡ በመጪዎቹ አመታት ውስጥ ምርቱን በተመለከተ ሊኖር የሚችለውን የገበያ ፍላጎት አውቆ መጠኑን
ለመተንበይና ለመወሰን ያስችለናል፡፡ ከጥናቱ በመነሳት የምርት ተጠቃሚ እንዲጨምር ምን መሰራት እንደሚኖርበት
ይጠቁመናል፡፡
1 Page 28 of 47
ፕሮጀክቱ ሊያመርት ላቀዳቸው ምርቶች የቀረበው የአመራረት ዘዴ እንዴት እንደተመረጠ ሌሎች አማራጮች የአመራረት
ዘዴዎች አብራርቶ በማስቀመጥ ተመራጭነቱን በግልፅ ማሳየት ያስፈልጋል፡፡
የቴክኖሎጂ አማራጮችን በማወዳደር ብቃት ያለውን ለመምረጥ ይቻል ዘንድ 1 ኛ/አዲስ መሳሪያ መትከል ወይስ ያለውን
ማሻሻል 2 ኛ/ቴክኒዎሎጂው በአመዛኙ የሰው ሃይል ወይስ ካፒታል የሚጠቀም ስለመሆኑ 3 ኛ/ ጥቅም ላይ የሚውለው
ቴክኒዎሎጂ የሚጠቀመው ጥሬ እቃ የሃገር ውስጥ ወይስ የውጪ 4 ኛ/ተመራጭ ቴክኖሎጂ በምርምር ያለፈ መሆኑንና
በተግባር የተፈተነ ስለመሆኑ ማረጋገጥ 5 ኛ/የቀረበው ቴክኖሎጂ ዋጋና የሚሰጠው ጥቅም 6 ኛ/ለሚሰራበት አካባቢ
አየር ፀባይ ተስማሚ መሆኑን ማረጋገጥ 7 ኛ/ቴክኖሎጂውን ለመጠቀም የሚያስፈልገው የስልጠና ፍላጎትና በዚያው
አቅም መጠገን ስለመቻሉ 8 ኛ/ ጊዜው ያላለፈበት/obsolete/ ላለመሆኑ ከአማራጭ ቴክኖዎሎጂ ጋር በማወዳደር
ተመራጭነቱን ማረጋገጥና፡፡ በተጨማሪም የቴክኒዎሎጂው የማምረት አቅም በቀን፤ በወርና በአመት ገምቶ አዋጭነቱን
በመረጃ አስደግፎ ማቅረብና ለወደፊት ያለውን የመስፋፋት ዕድል በማብራራት የአካባቢውን የገበያ ጥናት መሰረት
በማድረግ ወደ ምርጫ መሄድ ይቻላል፡፡
1 Page 29 of 47
እንደዚሁም አንድ ፕሮጀክት ሊያስገኝ ከሚችላቸው በርካታ ጥቅሞች ቢኖሩም ለአብነት ያህል ትርፋማነት፤ የስራ ዕድል
መፍጠር፤ የውጭ ምንዛሬ ማዳን ወይም ማስገኘት፤ የህዝቡን መሰረታዊ ፍላጎት ማርካት ወዘተ፡፡ ስለዚህ ፕሮጀክቱ
እንዲቀጥል ከተፈለገ ስለእያንዳዱ የፕሮጀክት አካሎች ስለሚያስከትሉት ወጪም ሆነ ገቢ ሳይንሳዊ በሆነ ዘዴ ተሰልተው
አዋጭነታቸው ሊታይ ይገባል፡፡
ስለዚህ ዓላማና ግብ ያለው የተቆጠረ ተግባራትን ያስቀመጠና የክትትልና ቁጥጥር ሥልት በማውጣት ፕሮጀክቱን መምራት
የሚችል አወቃቀር ስልት መከተል ያስፈልጋል፡፡
አንድን ፕሮጀክት በማዋቀር ደረጃ በአብዘሃኛው ሁለት አማራጮች ሊኖሩት ይችላል፡፡ ፕሮጀክቱ በድርጅቱ
/functional organization/ ውሰጥ እንዲመራ ማድረግና ስራዎቹን ማስፈፀም ወይም እራሱን ችሎ አዲስ
በሚቋቋም/pur project organization/ የፕሮጀክት መዋቅርና አመራር እንዲተዳደር ማድረግ ይቻላል፡፡ በአንድ
ፕሮጀክት ውስጥ ሊኖሩ የሚችሉትን የስራ መደብ
የሚከናወነው ተግባር ለይቶ ማስቀመጥና እያንዳዱ ክፍል ከሌላው ጋር ሊኖረው ስለሚችል ቅንጅት ትርጉም በሚሰጥ መልክ
ተብራርቶ ሊቀመጥ ይገባል፡፡
በፕሮጀክት አፈፃፀም ወቅት በአካባቢ የሚከሰቱ በጎና በጎ ያልሆኑ ሁኔታዎች ስለሚኖሩ አንድ ፕሮጀክት ወደ ተግባር
ከመለወጡ በፊት በቅድሚያ በአካባቢ የሚፈጠረውን ተፅዕኖ እንድናጠና እንገደዳለን፡፡
አንድ ፕሮጀክት ጥሬ ዕቃን በመጠቀምም ሆነ ተረፈ ምርት በማስወጣት በኩል አካባቢን መልሶ የሚጎዳ እንዳይሆን ጉዳቱን
ለመቀነስና ለማጥፋት የሚቻልበት ሁኔታ ማመቻቸት ተገቢ ይሆናል፡፡
ጉዳቱ የማይካካስ ወይም የማይቀረፍ ሆኖ በትውልድ ላይ መጥፎ ሁኔታ የሚፈጥር ወይም የሚያስከትል ከሆነ አማራጭ
የፕሮጀክት ሃሳቦችን እስከማየት መሄድ ይኖርብናል፡፡ በፕሮጀክቱ ሂደትና ውጤት በበጉ ሁኔታ የሚታይ ከሆነም
ጠቀሜታውን በሚገባ ማብራራትና ማሳወቅ ያስፈልጋል፡፡
1 Page 30 of 47
የዚህ ጥናት የመጀመሪያ ሥራ በህብረተሰቡ ማህበራዊ ሂደት ላይ ያተኮረ መሰረታዊ መረጃ በማሰባሰብና ሰፊ ጥናት
ማካሄድ ነው፡፡ ስለሆነም በዚህ ጥናት 4 ጉዳዮችን መመለስ መቻል አለብም፤
ምዘና በአመዛኙ አስፈላጊ ሁኖ የሚገኘው በባለንብረትነት ያስተዳድራል የተባለው አካል ወይም ለፕሮጀክቱ መመስረት
ድጋፍ የሚሆነውን አብዘሃኘውን የገንዘብ መጠን የሚያቀርቡ አካሎች ነው፡፡ የፕሮጀክት ምዘና/Appraisal/ ማለት
ተዘጋጅቶ የቀረበውን ፕሮጀክት ዝርዝር ሁኔታ በመመርመር በተግባር ሊተረጎም የሚችል መሆኑን አስፈላጊውን መመዘኛ
ማሟላቱን ማረጋገጥና ለቀጣይ ተግባር ማሳለፍ ነው፡፡ ይህም ሲባል የፕሮጀክት ዝግጅት ሰፊ ጥናት ከተደረገበት በኋላ
በአቅራቢው አካል በሰነድ ተዘጋጅቶ ለውሳኔ ሰጭ ክፍል ይቀርባል፡፡
የፕሮጀክቱ ሰነድ የቀረበለትም አካልም የፕሮጀክት ብቃት ግምገማ/Appraisal/ በሚያካሂድበት ወቅት ግምተ ውሥጥ
ሊያስገባ ከሚገቡ ጉዳዮች መካከል ዋነኞቹ የሚከተሉት ናው፡፡
የፕሮጀክቱ ይዘት ከአገሪቱ አጠቃላይ የልማት አቅጣጫ ጋር የሚጣጣምና የዘርፉ ፖሊሶዎችንና መመሪያዎችን
ያገናዘበ መሆኑን;
ተዘጋጅቶ የቀረበው ፕሮጀክት ለድርጅቱ አስፈላጊ መሆኑን
ፕሮጀክቱ በዝቅተኛ ወጭ አንገብጋቢ የድርጅቱን ችግሮች ለመፍታት ሌሎች አማራጮችን ማካተቱ፤
ፕሮጀክቱ የድርጅቱን ሃብት ጥቅም ላይ የማዋል ችሎታው
የፕሮጀክቱ ስፋትና መጠን ለማስተዳደር አመችነት ያለውና ከማስተዳደር አቅም ጋር መጣጣሙ
ፕሮጀክቱ በአካባቢ ስለሚኖረው ተፅዕኖ
1 Page 31 of 47
የፕሮጀክቱ ወጭ በትክክል መታወቁንና ለድርጅቱ የሚያስገኘው ጥቅም ከወጭ አንፃር ሲመዘን የበለጠ መሆኑን
ፕሮጀክቱ በጊዜ የመጣና ወቅታዊ መሆኑን የመሳሰሉት ናቸው፡፡
በፕሮጀክት ብቃት ግምገማ/Appraisal/ ወቅት ሌላው ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ የፋይናንስ ግምገማ ነው፡፡
በዚህ ወቅት መታየት የሚገባቸው ጉዳዮች
በተጨማሪም የፕሮጀክት ምዘና በሚካሄድበት ወቅት ተዘጋጅቶ የቀረበው ፕሮጀክት በተለያዮ ሌሎች መስፈርቶች ማለትም
2.4.የፕሮጀክት ትግበራ/Implementation/
የፕሮጀክት ተፈፃሚነት ደረጃ ተብሎ የሚታወቀው ክፍል ከፕሮጀክቱ የግምባታ ስራ ጀምሮ ፕሮጀክቱ በታለመለት መሰረት
ሙሉ በሙሉ የምርት ሂደት ወይም አገልግሎት የማቅረብ ደረጃ መድረስ እስከተቻለበት ድረስ ያለውን የሚያጠቃልል ነው፡፡
የፕሮጀክት አፈፃፀም ደረጃ ላይ
የፕሮጀክት አፈፃፀም ዲዛይንና የስራ ዝርዝር ግምት
የጨረታ ዶክመንቶች ማዘጋጀት
ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ማተሪያሎች ማዘጋጀት
ለፕሮጀክቱ አስፈላጊ የሆኑ ስምምነቶችናና ኮንትራቶችን መፈራረም
ለፕሮጀክቱ አስፈላጊ የሆኑ ሠራተኞችን መቅጠር ወዘተ የሚከናወኑበት ደረጃ ነው፡፡
አንድ ፕሮጀክት ተግባራዊ ለማድረግ ከታለመለት ግብ ለመድረስ እንዲቻል ዝርዝር የስራ መርሃ ግብር/action plan/
ሊነደፍ ይገባል፡፡ የፕሮጀክቱ የስራ መርሃ ግብር/action plan/
1 Page 32 of 47
የሚከናወነውን ሥራ ዓይነት፤ አስፈፃሚው አካል፤ ስራው የሚጠይቀው ጊዜ፤ ለስራው የሚያስፈልግ ወጭ፤ ስራው
የሚካሄድበትን ቦታና ጊዜ ወዘተ ሊያካትት ይችላል፡፡ ለምሳሌ፤
የስራ መርሃ ግብር የልማትና የአገልግሎት ፕሮጀክቶች ወይም ፕሮግራሞች መቼ? በማን? የት? እንዴት? እንደሚሰሩ
የሚጠቁም የስራ መመሪያ ሲሆን በአፈፃፀም ወቅትም ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን የሚዳስስና የተለያዮ አማራጭ
የአፈፃፀም፤ የክትትልና ግምገማ ስልተችን የሚያካትት ነው፡፡
አሳታፊ ክትትልና ግምገማ የፕሮጀክቱን ተጠቃሚዎችና ሌሎች ተሳታፊዎች(stakeholders) ባሳተፈ መልኩ አንድን
ፕሮጀክት ወይም ፕሮግራም ውቴታማነትና ተፅዕኖ ለመለካት የሚያስችል መረጃ የመሰብሰብና የመተንተን ሂደት ነው፡፡
ክትትልና ግምገማ የተሳሰሩ ሃሳቦች ቢሆንም የየራሳቸው ስልትና የትኩረት ነጥብ አላቸው፡፡ ክትትል/monitoring/
ተጨማሪ ውድቀት ሳይከተል ችግሮችን በወቅቱ ለማመልከት እና ለማስተካከል የሚያስችል መሳሪያ ነው፡፡ በሌላ መልኩ
ግምገማ/Evaluation/ አሁን እውን የሆነው ፕሮጀክት ቀደም ሲል በዝርዝር ጥናትና በሃሳብ ደረጃ በነበረበት ወቅት
ታልሞለት ነበረውን ዓላማና ግብ አሳክቷል ወይስ አላሳካም የሚል ነው፡፡ ይህም በአንድ ፕሮጀክት ተግባራዊ
ሂደት(process)፤ ውጤታማነትና አስተዋፅኦ ስልታዊ/systematic/ በሆነ አቀራረብ በተወሰነ ጊዜ ቆይታ
የሚታይበት መንገድ ነው፡፡
ግምገማ/Evaluation/ አንድ ፕሮጀክት ግምገማው ዓላማ በሂደት ላይ እያለ ወይም ከተጠናቀቀ በኃላ ሊሄድ የሚችል
ሲሆን ትኩረት የሚሰጠው ለፕሮጀክት ውጤት/ result or output/፤ እሴት /value/ እና ላስገኘው ተጨባጭ
ለውጥ/Impact/ ነው፡፡
1 Page 33 of 47
አሳታፊ የግምገማ ዘዴ ለልማት ፕሮጀክቶች ዉጤታማነት ዋነኛ መሳሪያ መሆኑን እዉቅና በማግኘቱ በአሁኑ መቅት በስፋት
እየተሰራበት ይገኛል፡፡ በፕሮጀክት ክትትል ግምገማና ሪፖርት ዝግጅት ወቅት ተጠቃሚው ክፍሎችና ሌሎች ተሳታፊ
አካላት ሚና እንዲኖራቸው ማድረግ ለፕሮጀክቶች ስኬትና ዘላቄታውነት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡
1 Page 34 of 47
መ. የግምገማ አይነቶች
1 Page 35 of 47
ሰንጠረዥ 1. የክትትልና ግምገማ ተያያዥነት፤
1 Page 36 of 47
ግምገማ መቼ ያስፈልጋል?
በክትትል ወቅት ያልተጠበቁ አሉታዊ /በጎ ውጤቶች መኖራቸውን የሚያመለክቱ ወይም የሚጠቁሙ ሁኔታዎች ሲታዮ
የፕሮጀክቱ የበላይ አመራር ሰጪ አካል ለውሳኔ የሚረዱ መረጃዎችን በሚፈለግበት ወቅት
በክትትል ወቅት መፈታት የሚገባቸው ቁልፍ ጥያቄዎችና ችግሮች መኖራቸው ሲጠቆም
አስቀድሞ በተወሰዱ ዋና ዋና ታሳቢዎች ላይ ወሳኝ የሆኑ ለውጦች ሲከሰቱ
ቁልፍ የሆኑ ተሞክሮዎችን ማውጣት አስፈላጊ በሚሆንበት ወቅት
በፕሮጀክት ተጠቃሚዎች/Beneficiaries/
የበላይ አመራር አካላት
በፕሮጀክቱ አስፈፃሚ አካላት
በፕሮጀክቱ ፈፃሚ ቡድን ወዘተ
የሪፖረት ባህሪያት
1 Page 37 of 47
የክትትልና ግምገማና ሪፖርት ሲዘጋጅ የሚከተሉትን ነጥቦች ከግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ ነው፡፡
1 Page 38 of 47
ተጠቃሎ ሲታይ
ለፕሮጀክቶች ወደ ተግባር መሸጋገሪያ ወሳኝ የሆኑ ቅድመ ዝግጅቶች በበቂ ደረጃ አለመከናወናቸው፤
የፕሮጀክቶች የተግባር መርሃ-ግብር(plan action) ከማስፈፀም ጋር በሚገባ ተገናዝበው በአፈፃፀም ሂደት
ሊከሰቱ የሚችሉ የአቅም ክፍተቶችን ለማስወገድ በሚያስችል መልኩ አለመዘጋጀት የተነሳ በፕሮጀክቶች
አፈፃፀም ላይ የራሳቸው የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያሳድሩ ይታያል፡፡
የክትትልና ግምገማ ሂደት ውስጥ ተሳትፎ የሚኖራቸው ክፍሎች በአጠቃላይ ስለ ክትትልና ግምገማ አስፈላጊነትና
አካሄድ ተገቢው ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ፤
የክትትልና ግምገማ ሂደት ውስጥ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን የማሰባሰብ፤ የማከማቸት፤ መተንተን፤
የማሰራጨትና ወጥነት እንዲኖረው የማድረግ ባህልን ማሳደግ፤
የክትትንና ግምገማ ሂደት ውስጥ ለሚከናወኑ መረጃን የማሰባሰብ፤ የማከማቸት፤
የመተንተንና የማሰራጨት ተግባራት የሚውሉ ዘዴዎች ወጥነትና ተከታታይነት እንዲኖራቸዉ ማድረግ፤
ለክትትልና ግምገማ መነሻ የሚሆነውን የፕሮጀክቱ ዓላማና ግብ፤ ይህንኑ ከዳር ለማድረስ የተዘጋጀውን
የድርጊት መርሃ ግብር መሰረት አድርጎ መነሳትና የክትትልና ግምገማውን ስራ በመረጃ ማስደገፍ፤
ክትትልና ግምገማ የሚካሄዱበትን ጊዜያት መወሰንና ከዚህ አንፃር መታየት የሚገባቸውን ጉዳዮች መለየት፤
በየወቅቱ የሚከናወኑ የክትትልና ግምገማ ስራዎችን የሚጠበቀውን ውጤት መወሰንና ይህንኑ በግልፅ
በማስቀመጥ፤ ስለዚህም ፕሮግራም አውጥቶ ለተግባራዊነቱ የተቻለውን እንቅስቃሴ ሁሉ ማድረግ፤
የክትትልና ግምገማ ትልቁ ጠቀሜታ የሚለካው ወቅታዊ በመሆኑና ተገቢውን ደረጃ ጠብቆ ሲገኝ ሲሆን በዚህ ረገድ
የሚመለከተውን ድጋፍ ለማግኘት እንዲቻል (feed back) ከጊዜና መታየት ከሚገባቸው ጉዳዮች አንፃር
እንዲሄዱ ማድረግ፤
በማጠቃለያ የግምገማ ስራ ውስጥ በአፈፃፀም ሂደት አዳዲስ አሰራር ስልቶች ምን ያህል የማስፈፀም አቅምን
እንዳሻሻሉ መቃኘትና ለዚህም በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱትን ሁሉ ማበረታታት፤
በማጠቃለያው የግምገማ ስርዓት ውስጥ በአፈፃፀም ሂደት የተገኙ አዳዲስ አሰራሮች በተመክሮነት ለመጠቀም
የሚያስችል የአሰራር ስርዓት መዘርጋተ፤
1 Page 39 of 47
ምዕራፍ ሦስት
3. የፕሮጀክት ቀረፃና ሪፖረት ፎርማት
3.1. አንድ ፕሮጀክት ቀረፃ(propozal) ሊያካትታቸው የሚገባቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-
I. ማውጫ(Table of content)
ገፁ ከሦስት ከበለጠ ማውጫ ሊዘጋጅለት ይገበዋል፡፡ ማውጫ ሁሉንም ምራፎችና ንዑስ ምዕራፎች ያሉበትን ገፅ
ባመላከተ መልኩ መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡
II. አጭር መግለጫ(Excutive Summary)
ከግማሽ ገፅ ያልበለጠ ሆኖ ለያካትታቸው የሚገባቸው ሃሳቦች፡-
ፕሮጀክቱ እንዲሰራ ያስገደደው ዋና ችግር
ፕሮጀክቱ የሚያመጣው ተፅዕኖ
ለችግሩ የተቀመጠ መፍተሄ
የፕሮጀክት አዋጭነት የሚያመላክት ግምገማ
ፕሮጀክቱ የሚያስገኘው ጥቅም
ፕሮጀክቱ የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠንና የሚወስደው ጊዜ መካተት አለባቸው፡፡
III. መግቢያ(Back Ground)
ከአንድ ገፅ ባልበለጠ መገለፅ ሲገባው የሚያካትታቸው ነጥቦች፡-
ፕሮጀክቱ የሚፈታው ችግር ምን እንደሆነ
ችግሩን ለምን መፍታት እንዳስፈለገው
ስለፕሮጀክቱ አጠር ያለ ማብራሪያ የሚሉትን ይይዛል፡፡
IV. ፕሮጀክቱ የሚመልሳቸው ችግሮች(Rationale)
ፕሮጀክቱ እንዲሰራ ምክንያት የሆኑ ነገሮች ተሰርተው መገለፅ አለባቸው በተጨማሪም የፕሮጀክቱ አጠቃላይ
ግብ ለአንባቢው ግልፅ በሆነ መንገድ መስፈር አለበት፡፡
V. የፕሮጀክቱ ዓላማ(project objective)
ፕሮጀክቱ ሊሰራበት የሚችሉ ዋናውንና ዝርዝር ዓላማዎች ለይቶ ማቅረብ አለበት፡፡ ይህም ፕሮጀክቱ
ሲጠናቀቅ ሊያስገኘው ይችላል ተብሎ የታሰበውን ወጤት መግለፅ ያስፈልጋል፡፡
VI. የፕሮጀክቱ መግለጫ(project Description):-
የፕሮጀክቱ ስያሜና ዓላማ
ጉዳዮን የሚያስረዳ ገለፃ
የፕሮጀክቱ ቀጣይነት
የፕሮጀክተ የሚተገበርበት ስልት
ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችና የፕሮጀክቱን የግዜ ሰሌዳ ከአስር ገፅ ባልበለጠ መገለፅ
አለበት፡፡
VII. የፕሮጀክቱ አመራርና አደረጃጀት(project management and
organization):-
ፕሮጀክቱን የሚመሩቱና የሚሳተፉ
የባለሙያዎችን ኃላፊነትና ተግባር
LOGO Form No.:
ኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበር OP/KTSC/044
KOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY
ማንዋል . Page No.:
Issue No
1 Page 40 of 47
ይህ ርዕስ የሚይዛቸው፡-
የስብሰባ ቃለ ጉባኤ፤ የስራ ጉብኝት፤ የማማከር ስራ መቸ እንደሚደረግና በስንት ጊዜ ልዮነት
እንደሚቀርብ
የክትትል ስራ የሚሰራበት ስልት
የግምገማ ዕቅድን
ፕሮጀክት እንዴት ለሚመለከታቸው ሪፖርት እንደሚደረግ
XIV. የፕሮጀክቱ ቀጣይነት(sustainability):
ፕሮጀክቱ የሚሰጠውን ጥቅም ዘላቂነት መገለፅ አለበት፡፡
1 Page 41 of 47
ይህም የሚያካትታቸው፡-
I. የጥናቱ ርዕስ(Topic)
በርዕስ ገፅ ላይ የሚኖሩ ቃላት በጥንቃቄ መመረጥና ቃላቱም የተመጠኑ እና ጥናቱን በደንብ የሚገልፁ መሆን
አለባቸዉ፡፡
በዚህ ክፍል ዉስጥ መካተት የሚገባቸው ነገሮች፡-
የጥናቱ ርዕስ
የአጥኝዎቹ ሰምና አድራሻ
ጥናቱ የሚቀርብለት ድርጅት
የጥናቱ ፕሮፖዛል የሚቀርብበት ቀንና አመት
II. ምስጋና(Acknolodgement)
ጥናቱ ሲካሄድ ለአጥነው በገንዘብ፤ በማማከር፤ አጥኒውን በማበረታታት እና የተለያዮ ድጋፍ በማድረግ ጥናቱ
እንዲሳካ ለተባበሩን ሁሉ ስማቸውን በመግለፅ ምስጋና የሚገለፅበት ነው፡፡
III. ማውጫ(Table of content)
ማውጫ አንባቢዎች ማንበብ የሚፈልፉትን ክፍል በቀላሉ እንዲያገኝት የሚረዳ ክፍል ነው፡፡ማውጫ ሁሉንም ርዕሶችና
ንዕስ ርዕሶች እስከሚኙበት ገፅ ጭምር ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡
IV. ምስልና ሰንጠረዥ ማውጫ(Lists of figure and tables)
ይህ በአማርጭነት የሚያዝ ነው ጥናቱ በዛ ያሉ ስዕላዊ መግለጫና ሰጠረዥ ከያዘ ብቻ የምንጠቀምበት ነው፡፡
በዚህ ውስጥ የተጠቀምንባቸውን ስእላዊ መግለጫዎችና ሰንጠረዞችን ስማቸውንና የሚገኙበትን ገፅ ጭምር
በግልፅ መቀመጥ አለበት፡፡
V. ሙዳየ ቃል(Nominiclature)
ይህ እንደ አስፈላጊነቱ የሚገባ ሲሆን ብዙ ምፃረ ቃሎች ከተጠቀምን ምህፃረ ቃሎቻቸውና ትርጉማቸውን
ማስቀመጥ ያስፈልጋል፡፡
VI. አጭር መግለጫ(Abstract)
ይህ ክፍል ውስጥ ስለፕሮጀክቱ አጠቃላይ የሚገለፅበት ነው፡፡ ይህም ከአንድ መቶ እስከ ሁለት መቶ ቃላት
ሊይዝ ይችላል፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ መካተት ያለባቸው፡-
የፕሮጀክቱ መነሻ ሃሳብ፤ ችግርና የሚያስገኘው ጥቅም
በአጭርና በግልፅ ፕሮጀክቱ ለመስራት የተጠቀምንበት መንገድ
ዋና ዋና የፕሮጀክቱን ውጤቶችና ግኝቶች
የፕሮጀክቱ ማጠቃለያ
1 Page 42 of 47
ይህ ክፍል በፕሮጀክቱ ውስጥ የተሰሩትን ስራዎች፤ የፕሮጀክቱ የተጠቀመባቸው ቁሳቁሶችና አጠቃላይ የፕሮጀክቱ
የሚገለፅበት ነው፡፡ በዚህ ርዕስ ውስጥ መካተት የሚገባቸው ርዕሶች እንደ ሪፖርቱና አይነት የሚለያይ ቢሆንም
በመሰረታዊነት የሚከተሉትን ማካተት አለባቸው፡፡
ይህ ርዕስ ከማጠቃለያው ጋር በቀጥታ መገናኘት አለበት በተጨማሪም ለተጨማሪ ስራ የሚሆኑ ሃሳቦችን ማካተት አለበት፡፡
በአጠቃላይ ይህ ርዕስ በጥናቱ ግኝቶች ላይ የራሳቸውን ተፅእኖ ለሚያሳድሩ አካላት ትልቅ የሆነ ድርሻ አለው፡፡
X. አባሪ(Appendices)
ፕሮጀክቱን ለማካሄድ የተጠቀምናቸውን መረጃዎች ማለትም መጠይቆች፤ የተለያዮ ፕሮግራሞች እና ሌሎች ፎርማቶች
ከጥናቱ ጋር ተያይዘው የሚቀርቡበት ነው፡፡
XI. ማጣቀሻ(Reference)
በዚህ ክፍል የጥናቱን እውነተኛነት ይመለከትበታል፤ የተጠቀምናቸው የመረጃ ምንጮች በማን ፤ መቼ እንደፃፉና የመረጃ
መረቡ ስም በግልፅ መቀመጥ አለበት፡፡
1 Page 43 of 47
ክፍል 3
የጥናትና የፕሮጀክት
አተገባበር
LOGO Form No.:
ኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበር OP/KTSC/044
KOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY
ማንዋል . Page No.:
Issue No
1 Page 44 of 47
ምዕራፍ 1
የተሰሩ ስራዎችን የሚገልፅ፤ የሚሰሩ ስራዎችን የሚያመላክቱ ሪፖርቶች፤ የሚቀረፁ ፕሮፖዛሎች በሚመለከታቸው መቅረብ
ይኖርባቸዋል፡፡
እንደ ጥናትና ፕሮጀክት ስራው ስፋት አንፃር በመከፋፈል ፕሮግረስ ርፖርት በየደረጃው ለሲስተምና ደንበኞች
አገልግሎት ማሻሻያ አገልግሎት ለአስተያየት ይቀርባል፡፡ በተሰጠው አስተያየት መሰረት ማስተካከያ በማድረግ
በቀጣይ በሚደረገው ፕሮግረስ ሪፖርት ወይም
1 Page 45 of 47
የመጨረሻ ሪፖረት በማቅረብ በአጠቃላይ ስራው ላይ በተሰጠው አስተያየት ማስተካከያ በማድረግ የመጨረሻውን
የጥናት/ፕሮጀክት ስራ ውጤት ይቀርባል፡፡
አንድ ጥናት/ፕሮጀክት ወደ ተግባር ተለውጦ እያገለገለ ባለበት ሁኔታ ማሻሻል ቢያስፈልግ በሚከተለው መንገድ መከናወን
ይኖርበታል፡፡
ጥናቱ/ፕሮጀክቱ ለምን መሻሻል እንዳለበት የሚያመላክት ዝርዝር መረጃ ከስራው የመጨረሻ ተጠቃሚዎች፤ ወይም
ጥናቱን ወይም ፕሮጀክቱን ከሰራው/ከሰሩት ይቀርባል፤
መሻሻሉ አሳማኝ ሁኖ ሲገኝ የማሻሻያ ፕሮፖዛል ለሲስተምና ደንበኞች አገልግሎት ማሻሻያ አገልግሎት
ይቀርባል፡፡
የማሻሻያ ስራው ቀደም ሲል የጥናቱ/ፕሮጀክቱን በሰራው/በሰሩት በተጨማሪም ስለፕሮጀክቱ ጥሩ ግንዛቤ ባላቸው
ሰዎች ይከናወናል፡፡
በማሻሻው ስራው ላይ እንደአስፈላጊነቱ ስልጠናና የአጠቃቀም ማንዋል ይዘጋጃል፤
የማሻሻው ስራው አጠቃላ ውጤት ለሲስተምና ደንበኞች አገልግሎት ማሻሻያ አገልግሎት ይቀርባል፡፡
V. ወደ ተግባረ በተለወጠ ጥናት/ፕሮጀክት የሚያጋጥም ችግር/Failure/መፍታትን በተመለከት
አንድ ጥናት/ፕሮጀክት ወደ ተግባር ተለውጦ እያገለገለ እያለ ችግር ቢያጋጥመው በሚከተለው መንገድ ሊፈታ
ይችላል፡፡
1 Page 46 of 47
1 Page 47of 47
ማጣቀሻ ( Refrence)
1.የፕሮጀክት ዕቅድ አዘገጃጀት ክትትልና ግምገማ አሰራር, በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ,
ባህርዳር, ሰኔ 1999 ዓ.ም .
2. Research proposal - Wikipedia, the free encyclopedia
en.wikipedia.org/wiki/Research_proposal
3. What is research proposal? definition and meaning
www.businessdictionary.com/definition/research-proposal.html
4. Writing a Research Paper - Purdue OWL
https://owl.english.purdue.edu/owl/owlprint/658/
5. What Is a Project Proposal?
www.wisegeek.com/what-is-a-project-proposal.htm
6. steps to writing a successful project proposal - University of Lethbridge
www.uleth.ca/education/sites/.../files/Steps_to_Project_Proposal.pdf
7. Format for project reports
carmaux.cs.gsu.edu/~mweeks/project.html
8.format for preparation of project report - Anna University
www.annauniv.edu/academic/ug_format.doc
LOGO Form No.:
ኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበር OP/KTSC/044
KOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY
. Page No.:
Annex A (document writing templet) Issue No
Page 1 of 1
1
ISSUE HISTORY
Issue Discription of Originator Effective Date
Change
1 Initial Realease Negusie mulat
Meseret
genetu
Keder zewedu
Hiwot yimer
REFERENCE DOCUMENT
Document Number Document Title
FOR DOCUMENT
CONTROLUSE ONLY
APPROVAL Name: Signature: Date:
1 Page 1 of 1
ቁጥር…………….
ቀን……………….
በ 2005 በጀት ዓመት በሁለተኛ ሩብ ዓመት በያዝነው መርሃ-ግብር መሰረት የምርምርና ስርፀት አሰራር መመሪያ ማንዋል
አዘጋጅተን የላክን መሆኑን እየገለፅን ታይቶ እንዲፀድቅልን እንጠይቃለን፡፡
ከሠላምታ ጋር