ለAndroid ተኳዃኝ የሆነ አካላዊ የቁልፍ ሰሌዳ መግዛት እና ከእርስዎ ጡባዊ ጋር ማገናኘት ይችላሉ። ይህ በፍጥነት ሰነዶችን እንዲያዋቅሩ፣ ኢሜይሎችን እንዲጽፉ እና የእርስዎን ጡባዊ በይነገፅ እንዲያስሱ ያስችልዎታል።
አስፈላጊ፦ ከእነዚህ እርምጃዎች ላይ አንዳንዱ የሚሠሩት Android 14 ወይም ከዚያ በላይ በሆኑት ላይ ብቻ ነው። እንዴት የAndroid ሥሪትዎን እንደሚያዘምኑ ይወቁ።
ከእርስዎ ጡባዊ ጋር አካላዊ የቁልፍ ሰሌዳ ያገናኙ
ከእርስዎ ጡባዊ ጋር ብሉቱዝ የቁልፍ ሰሌዳ ለማገናኘት፦
- የቁልፍ ሰሌዳውን በማጣመር ሁነታ ውስጥ ያድርጉ። ለእገዛ የቁፍ ሰሌዳ አምራች መመሪያዎችን ዋቢ ያድርጉ።
- የመሣሪያዎን ቅንብሮች
ይክፈቱ።
- ቅንብሮች
የተገናኙ መሣሪያዎች
አዲስ መሣሪያ ያጣምሩ ላይ መታ ያድርጉ።
- ከሚገኙ መሣሪያዎች ቀጥሎ ማገናኘት የሚፈልጉት የቁልፍ ሰሌዳ ላይ መታ ያድርጉ።
አካላዊ የቁልፍ ሰሌዳዎ ቅንብሮችን ይለውጡ
- የመሣሪያዎን ቅንብሮች
ይክፈቱ።
- ሥርዓት
የቁልፍ ሰሌዳ
አካላዊ የቁልፍ ሰሌዳ ላይ መታ ያድርጉ።
- «አካላዊ የቁልፍ ሰሌዳ» ከሚለው ስር፦
- አካላዊ የቁልፍ ሰሌዳ አቀማመጡን ይለውጡ፦ የእርስዎን የአሁን አካላዊ የቁልፍ ሰሌዳ ይምረጡ
አቀማመጡን መለወጥ የሚፈልጉበትን ቋንቋ ይምረጡ
አቀማመጥ ይምረጡ።
- አካላዊ የቁልፍ ሰሌዳ አቀማመጡን ይለውጡ፦ የእርስዎን የአሁን አካላዊ የቁልፍ ሰሌዳ ይምረጡ
- «አማራጮች» ከሚለው ስር ቅንብር ይለውጡ፦
- ታይታ የቁልፍ ሰሌዳ ይጠቀሙ፦ አካላዊ የቁልፍ ሰሌዳ ገቢር ሲሆን በጡባዊው ማያ ገፅ ላይ የእርስዎን ምናባዊ የቁልፍ ሰሌዳ ለማቆየት ከፈለጉ ይህን ያብሩ።
- የቁልፍ ሰሌዳ አቋራጮች፦ ጠቃሚ የቁልፍ ሰሌዳ አቋራጮች ዝርዝር ለማሳየት መታ ያድርጉ።
- የአሻሻይ ቁልፎች፦ እንደ Caps lock፣ Ctrl እና Alt ያሉ አካላዊ የቁልፍ ሰሌዳ ቁልፎች ባህሪን ለመለወጥ ይህን ቅንብር መታ ያድርጉ።
ጠቃሚ ምክር፦ አካላዊ የቁልፍ ሰሌዳዎን ከእርስዎ ጡባዊ ጋር ካገናኙ በኋላ ለእርስዎ ታይታ የቁልፍ ሰሌዳ ያሉ የቋንቋ ቅንብሮች በራስ-ሰር ይተገበራሉ።
የመዳሰሻ ሰሌዳ ቅንብሮችን ይለውጡ
አካላዊ የቁልፍ ሰሌዳዎ የመዳሰሻ ሰሌዳ ካለው ከእርስዎ ጡባዊ ጋር ካገናኙት በኋላ የመዳሰሻ ሰሌዳውን ቅንብሮች ሊያስተካክሉ ይችላሉ፦
- የመሣሪያዎን ቅንብሮች
ይክፈቱ።
- ሥርዓት
የመዳሰሻ ሰሌዳ ላይ መታ ያድርጉ።
- ቅንብር ይለውጡ፦
- ጠቅ-ለማድረግ-መታ-ያድርጉ፦ ይህ ቅንብር ሲበራ፣ ለመምረጥ በመዳፊት ላይ ከግራ ጠቅታ ጋር ተመሳሳይ የሆነውን የመዳሰሻ ሰሌዳዎን መታ ማድረግ ይችላሉ።
- የተገላቢጦሽ ማሸብለል፦ ወደታች ሲያሸበልሉ ይዘት ወደላይ እንዲሄድ ለማድረግ ያብሩ።
- የግርጌ-ቀኝ መታ ማድረግ፦ የመዳሰሻ ሰሌዳዎን የግርጌ-ቀኝ ጥግ መታ ሲያድርጉ ተጨማሪ አማራጮችን ለመድረስ ያብሩ።
- የጠቋሚ ፍጥነት፦ ፍጥነት ለመለወጥ ወደ ግራ እና ቀኝ ይጎትቱ።