ለፈጣሪዎች እና የይዘት ባለቤቶች በጣም ጠቃሚ በሆኑ መሣሪያዎች የይዘትዎን አፈጻጸም ለመለካት ትንታኔዎን ይድረሱ። YouTube ላይ ያለ ትንታኔ በመጠቀም አፈጻጸም ለመለካት እንዴት ውሂብ መጠቀም እንደሚችሉ ይወቁ።
ትንታኔዎን ይድረሱ
ማስታወሻ፦ ብዙ መለያዎች ካሉዎት ማስተዳደር የሚፈልጉት መለያ ውስጥ እንደገቡ ያረጋግጡ።
- ወደ YouTube ስቱዲዮ ይግቡ።
- ከግራ ምናሌው ትንታኔ
የሚለውን ጠቅ ያድርጉ።
ለፈጣሪዎች ውሂብ
- YouTube ትንታኔ፦ እንደ ፈጣሪ የእርስዎን ቪድዮ እና የሰርጥ አፈጻጸም ከቁልፍ መለኪያዎች እና ሪፖርቶች ጋር በተሻለ ለመረዳት YouTube ትንታኔን መጠቀም ይችላሉ። የበለጠ ለመረዳት።
- YouTube ትንታኔ ለአርቲስቶች፦ ለሙዚቃ ይዘትዎ በተለየ የተነደፈ ትንታኔን ለማየት YouTube ትንታኔ ለአርቲስቶችን መጠቀም ይችላሉ። የበለጠ ለመረዳት።
የይዘት ባለቤቶች ውሂብ
- ለስቱዲዮ ይዘት አስተዳዳሪ YouTube ትንታኔ፦ ለYouTube ስቱዲዮ ይዘት አስተዳዳሪዎች በጣም ጠቃሚ የሆኑን መለኪያዎች እና ባህሪያት የሚያደምቁ የእርስዎ ቪድዮዎች፣ ሰርጦች እና ንብረቶችን አፈጻጸም መከታተል ይችላሉ። የበለጠ ለመረዳት።
- የYouTube ሊወርዱ የሚችሉ ሪፖርቶች፦ የይዘትዎን አፈጻጸም ሪፖርቶች እና ሌሎችንም ማውረድ ይችላሉ። የበለጠ ለመረዳት።
የYouTube ትንታኔ ኤፒአዮች
የYouTube ትንታኔ ኤፒአይ እና የYouTube ሪፖርት ማድረጊያ ኤፒአይ የYouTube ትንታኔ ውሂብ መዳረሻ ያቀርባሉ። ለመተግበሪያዎ ትክክለኛውን ኤፒአይ እንዲመርጡ ተመሳሳይነት እና ልዩነቶችን ይረዱ። የበለጠ ለመረዳት።
- የYouTube ትንታኔ ኤፒአይ፦ የYouTube ትንታኔ ኤፒአይ ብጁ የYouTube ትንታኔ ሪፖርቶችን ለማመንጨት የእውነተኛ ጊዜ ዒላማ ጥያቄዎችን ይደግፋል። የበለጠ ለመረዳት።
- የYouTube ሪፖርት ማድረጊያ ኤፒአይ፦ የYouTube ሪፖርት ማድረጊያ ኤፒአይ ለሰርጥ ወይም ይዘት ባለቤት የYouTube ትንታኔ ውሂብ የሚይዙ የጅምላ ሪፖርቶችን ያመጣል። የበለጠ ለመረዳት።