ማያ ገጽዎን ለመፈለግ ክበብ በሚለው ይፈልጉ

አስፈላጊ፦ ይህ ባህሪ በተመረጡ የAndroid ስልኮች ሞዴሎች ላይ ይገኛል።

Google ላይ እነሱን ለመምረጥ እና ለመፈለግ በማያ ገጽዎ ማንኛውም ቦታ ላይ ጽሑፍ ወይም ምስሎች ላይ ያክብቡ፣ ያድምቁ፣ ይጻፉ ወይም መታ ያድርጉ።

ለመፈለግ ክበብን እንዴት እንደሚጠቀሙ

በማያ ገጽዎ ላይ ጽሑፍ፣ ምስሎች ወይም ቪድዮዎችን ለመፈለግ፦

  1. ለመፈለግ ክበብ ይጀምሩ፦
    • ባለ3-አዝራር ዳሰሳ ሁነታ ላይ የመነሻ አዝራሩን በረዥም ይጫኑ።

    • የእጅ ምልክት ዳሰሳ ሁነታ ላይ የአሰሳ መያዣውን በረዥም ይጫኑ።

    እንዴት በAndroid ስልክዎ ላይ እንደሚንቀሳቀሱ ይወቁ።

  2. መፈለግ የሚፈልጉትን ጽሑፍ፣ ምስል ወይም ቪድዮ ለመምረጥ በማያ ገጹ ማንኛውም ቦታ ላይ ያክብቡ፣ ያድምቁ ወይም መታ ያድርጉ።
  3. ከተፈለገ የፍለጋ አሞሌው ውስጥ ጽሑፍ በማከል ፍለጋዎን ማጥራት ይችላሉ።
  4. የፍለጋ ውጤቶችዎ በማያ ገጹ ግርጌ ላይ ይታያሉ።
    • ተጨማሪ ውጤቶችን ለማየት ውጤቶች ላይ ወደላይ ያንሸራትቱ።

ጠቃሚ ምክሮች፦

  • ምርጫዎን ለማስተካከል የምርጫውን ክፈፎች ወይም ሙሉ ምርጫውን ይጎትቱ።
  • በፍለጋ አሞሌ ከታገደ ይዘት ጋር መስተጋብር ለመፍጠር መስኮቱን ለማንቀሳቀስ በሁለት ጣት ያንፋቅቁ ወይም የፍለጋ አሞሌውን ወደ ማያ ገጹ አናት ወይም ግርጌ ይጎትቱ።
  • ሙሉ ማያ ገጽዎን በቅጽበት ለመተርጎም ከፍለጋ አሞሌው ቀጥሎ የመተርጎሚያ አዝራሩ ላይ መታ ያድርጉ። ይህ ባህሪ ለተመረጡ መሣሪያዎች ይገኛል።
  • በእርስዎ ዙሪያ ወይም በመሣሪያዎ ላይ ባሉ ድምፅ ማውጫዎች ላይ ለሚጫወተው ኦዲዮ የሙዚቃ ፍለጋን ለማከናወን የሙዚቃ ምልክቱን መታ ያድርጉ።
  • በመላው ማያ ገጽ ላይ ፍለጋ ለማከናወን ለመፈለግ ክበብ የሚለውን ይክፈቱ እና የፍለጋ አሞሌውን መታ ያድርጉ።
  • አንድ ቅጽበታዊ ገጽ ዕይታን ከጥያቄው ለመሰረዝ የቅጽበታዊ ገጽ ዕይታውን ምስል በትንሹን ሁለቴ መታ ያድርጉ ወይም በቁልፍ ሰሌዳዎ ላይ ያለውን የኋሊት መደምሰሻ ይጫኑ።

ለመፈለግ ክበብ በሚለው የሰው ሠራሽ አስተውሎት አጠቃላይ ዕይታዎችን ያግኙ

በጽሑፍዎ ወይም ባለብዙ ፍለጋ መጠይቆች መሰረት የሰው ሠራሽ አስተውሎት አጠቃላይ ዕይታዎችን ለመፈለግ ክበብ በሚለው ማግኘት ይችላሉ። ስለ ባለብዙ ፍለጋ የበለጠ ይወቁ

ለመፈለግ ክበብን ያጥፉ

ባለ3-አዝራር ዳሰሳ ሁነታ ላይ

  1. በእርስዎ Android ስልክ ላይ ወደ ቅንብሮችSettings ይሂዱ።
  2. ለመፈለግ ክበብ ብለው ይፈልጉ።
  3. ለመፈለግ ክበብ ላይ መታ ያድርጉ።
  4. ለመፈለግ ክበብ ያጥፉ።

የእጅ ምልክት ዳሰሳ ሁነታ ላይ

  1. በእርስዎ Android ስልክ ላይ ወደ ቅንብሮችSettings ይሂዱ።
  2. ለመፈለግ ክበብ ብለው ይፈልጉ።
  3. ለመፈለግ ክበብ ላይ መታ ያድርጉ።
  4. ለመፈለግ ክበብ ያጥፉ።

«ለመፈለግ ክበብ አይገኝም» ለሚለው ስሕተት መላ ይፈልጉ

በሚደገፍ Android መሣሪያ ላይ ለመፈለግ ክበብን ለመጠቀም የሚከተሉትን ያረጋግጡ፦

የፈቃዶች ቅንብሮችዎ ትክክል መሆናቸውን

  1. በእርስዎ Android ስልክ ላይ ወደ ቅንብሮችSettings ይሂዱ።
  2. ዲጂታል ረዳት መተግበሪያ ብለው ይፈልጉ።
  3. ዲጂታል ረዳት መተግበሪያ ላይ መታ ያድርጉ።
    • የሚከተሉትን ያረጋግጡ፦
      • ነባሪ ዲጂታል ረዳት ወደ «Google» መቀናበሩን።
      • «ቅጽበታዊ ገጽ ዕይታ ተጠቀም» መብራቱን።

የእርስዎ የGoogle መተግበሪያ ወቅታዊ መሆኑን

  1. በእርስዎ የAndroid ስልክ ላይ የGoogle Play መደብር መተግበሪያውን Google Play ይክፈቱ።
  2. በላይኛው ቀኝ በኩል፣ የእርስዎ የመገለጫ አዶ ላይ መታ ያድርጉ።
  3. መተግበሪያዎችን እና መሣሪያን አስተዳድር እና ከዚያ አስተዳድር ላይ መታ ያድርጉ።
  4. የGoogle መተግበሪያ Google Search ላይ መታ ያድርጉ።
    • «ዝማኔ ይገኛል» የሚለውን መሰየሚያ ከተመለከቱ አዘምን ላይ መታ ያድርጉ።

ተዛማጅ ግብዓቶች

ይሄ አጋዥ ነበር?

እንዴት ልናሻሽለው እንችላለን?

ተጨማሪ እገዛ ያስፈልግሃል?

እነዚህን ቀጣይ እርምጃዎች ይሞክሩ፦

ፍለጋ
ፍለጋ አጽዳ
ፍለጋን ዝጋ
ዋናው ምናሌ
11805948017515443749
true
የእገዛ ማዕከልን ይፈልጉ
true
true
true
false
false
false
false