የWhatsApp ውይይቶች እና ውሂብን ከእርስዎ የድሮ iPhone ወይም Android ወደ አዲስ Android መሣሪያ ማስተላለፍ ይችላሉ።
ምን እንደሚያስፈልግዎ
- የWhatsApp ምትኬ የነቃለት የድሮ ስልክዎ ወይም የድሮ ስልክዎ
- አዲሱ Android ስልክዎ
- የተረጋጋ የበይነመረብ ግንኙነት
አስፈላጊ፦
- ይህ ገፅ እንዴት WhatsApp ውይይቶች እና ውሂብን ወደ አዲስ Android መሣሪያ ማስተላለፍ እንደሚቻል መመሪያዎች አሉት። ለሌሎች ሥርዓተ ክወናዎች ወይም መሣሪያዎች ላይሠሩ ይችላሉ።
- የእርስዎ ውይይቶች እና ውሂብ ማስተላለፍ በተሳካ መልኩ እንደሚተላለፍ በWhatsApp ዋስትና አይሰጠውም። ማናቸውም ጥያቄዎች ወይም ስጋቶች ካሉዎት WhatsApp ድጋፍን ያነጋግሩ።
የWhatsApp ውሂብን ከAndroid መሣሪያ ላይ ያስተላልፉ
ከAndroid መሣሪያ ላይ ወደ አዲስ Android መሣሪያ ውሂብ ለማስተላለፍ፦
እርምጃ 1፦ የWhatsApp ውሂብዎን በGoogle መለያዎ ላይ ምትኬ ያስቀምጡ
- በድሮ Android መሣሪያዎ ላይ WhatsApp ይክፈቱ።
- ከላይ ከቀኝ በኩል ተጨማሪ
ላይ መታ ያድርጉ።
- ቅንብሮች
ውይይቶች
የውይይት ምትኬ ላይ መታ ያድርጉ።
- ምትኬ አስቀምጥ ላይ መታ ያድርጉ።
እምርጃ 2፦ በአዲሱ መሣሪያዎ ላይ WhatsApp ይጫኑ።
አስፈላጊ፦ ከድሮ መሣሪያዎ ላይ ወደ አዲሱ የእርስዎ Android መተግበሪያዎችን አስተላልፈው ከሆነ WhatsApp በአዲሱ መሣሪያዎ ላይ ተጭኖ መሆን አለበት።
WhatsApp ካልተጫነልዎት፦
- ወደ Play መደብር መተግበሪያ
ይሂዱ።
- WhatsApp ያውርዱ።
- በቀድሞ መሣሪያዎ ላይ በተጠቀሙበት ተመሳሳይ ስልክ ቁጥር ወደ WhatsApp ይግቡ።
እርምጃ 3፦ WhatsApp ውሂብዎን ከምትኬ ላይ ወደነበረበት ይመልሱ
ውሂብዎን ወደነበረበት እንዲመልሱ ሲጠየቁ ሁለት ምርጫዎች ይሰጡዎታል፦
- በWi-Fi አማካኝነት ወደነበረበት ለመመለስ ከድሮ ስልክ ላይ አስተላልፍ ላይ መታ ያድርጉ።
- በደመና አማካኝነት ወደነበረበት ለመመለስ ከምትኬ ላይ ወደነበረበት መልስ ላይ መታ ያድርጉ።
ጠቃሚ ምክሮች፦
- በርካታ Google መለያዎች ካሉዎት በመሣሪያዎችዎ ላይ ወደ ተመሳሳይ መለያ መግባትዎን ያረጋግጡ።
- የተዘመነ የደመና ምትኬ ካለዎት በደመና አማካኝነት ወደነበረበት መመለስ ይመከራል።
መላ ፍለጋ
WhatsAppን ወደነበረበት ለመመለስ በሚሞክሩበት ጊዜ ምትኬ ማግኘት አልቻሉም- በሁለቱም የድሮ እና አዲስ መሣሪያዎችዎ ላይ ወደ ተመሳሳይ Google መለያ መግባትዎን ያረጋግጡ።
- በድሮ መሣሪያዎ ላይ WhatsApp ውስጥ ምትኬ መንቃቱን እና መሄዱን ያረጋግጡ። በእርስዎ መሣሪያ ላይ እንዴት ውሂብ ማስቀመጥ እንደሚቻል ይወቁ።
- በአዲሱ መሣሪያዎ ላይ WhatsAppን ይዝጉ እና እንደገና ያዋቅሩ።
- በድሮ መሣሪያዎ ላይ WhatsApp ለመጨረሻ ጊዜ ምትኬ የተቀመጠለት መቼ እንደሆነ ይፈትሹ።
- ምትኬ ማስቀመጥን ወደ አይ ያቀናብሩ።
- እንደገና ወደነበረበት መመለስ ከፈለጉ በአዲሱ መሣሪያዎ ላይ ለWhatsApp የመተግበሪያ ውሂብን ይጥረጉ።
- WhatsApp ይክፈቱ።
- የማያ ገፅ ላይ መመሪያዎቹን ይከተሉ።
ጠቃሚ ምክር፦ በአዲሱ መሣሪያዎ ላይ የደረሱ ማናቸውም አዳዲስ መልዕክቶች ይጠፋሉ።
- በድሮ መሣሪያዎ ላይ WhatsApp ለመጨረሻ ጊዜ ምትኬ የተቀመጠለት መቼ እንደሆነ ይፈትሹ።
- WhatsApp የድሮ ምስሎችን ወደነበሩበት ለመመለስ የተወሰነ ጊዜ ሊወስድ ይችላል።
- ከ24 ሰዓታት በኋላ ካልታዩ WhatsApp ድጋፍን ያነጋግሩ።
- በአዲሱ መሣሪያዎ ላይ WhatsApp ከተጫነ ይፈትሹ።
- መሣሪያዎ በነባሪ WhatsApp ተጭኖለት ላይሆን ይችላል።
- WhatsApp ካልተጫነ ወደ Play መደብር ይሂዱ።
- WhatsApp ይጫኑ።
አስፈላጊ፦ በአዲስ ስልክ ላይ የተፈጠረ የውይይት ታሪክን በድሮ ስልክዎ ላይ ከተፈጠረ የውይይት ታሪክ ጋር ማዋሃድ አይችሉም። የድሮ የውይይት ታሪክዎን ወደነበረበት ከመለሱ በአዲሱ ስልክዎ ላይ የፈጠሩትን ማንኛውም የውይይት ታሪክ ይተካል።
የድሮ የመልዕክት ታሪክዎን ለማግኘት፦
- በአዲሱ መሣሪያዎ ላይ WhatsAppን ያራግፉ፦
- በአዲሱ መሣሪያዎ ላይ WhatsAppን እንደገና ይጫኑ።
የWhatsApp ውሂብዎን ወደ አዲስ ስልክ ቁጥር ማስተላለፍ አይችሉም። ሆኖም ግን ወደ አዲሱ ስልክዎ ከማስተላለፍዎ በፊት በድሮ መሣሪያዎ ላይ ያለውን ስልክ ቁጥር ወደ አዲሱ ስልክ ቁጥርዎ መለወጥ ይችላሉ።
ጠቃሚ ምክር፦ ሌሎች የውሂብ ስደት መተግበሪያዎች አይደገፉም እና የስደት ችግሮችን ሊፈጥሩ ይችላሉ። WhatsApp በማስተላለፍ ወቅት ውሂብዎን አይሰርዝም እና ችግር ከተከሰተ ውሂብዎ አይጠፋም።