በደህንነት ባህሪያት ውሂብዎን እና መሣሪያዎን በመጠበቅ የስልክ ስርቆትን ተጽዕኖ ይቀንሱ።
አስፈላጊ፦ የድሮ የAndroid ሥሪት እየተጠቀሙ ነው። አንዳንዶቹ እነዚህ እርምጃዎች የሚሠሩት Android 15 እና ከዚያ በላይ በሆኑት ላይ ብቻ ነው። የAndroid ሥሪትዎን ይፈትሹ።
የስርቆት ጥበቃ
አስፈላጊ፦
- ከእነዚህ እርምጃዎች አንዳንዶች የሚሠሩት Android 10 እና ከዚያ በላይ ላይ ብቻ ነው። የAndroid ሥሪትዎን እንዴት እንደሚፈትሹ ይወቁ።
- እነዚህ ባህሪያት በAndroid Go መሣሪያዎች፣ ጡባዊዎች እና ተለባሾች ላይ አይደገፉም። እንዲሁም ድጋፍ በእርስዎ ዘመናዊ ስልክ መሣሪያ ሞዴል መሠረት ሊለያይ ይችላል።
- እነዚህን ባህሪያት በሚደገፍ መሣሪያ ላይ ለማብራት መሣሪያው የማያ ገፅ ቁልፍ ማቀናበር አለበት። የAndroid መሣሪያ ላይ እንዴት ማያ ገፅ መቆለፊያ እንደሚያቀናብሩ ይወቁ።
Theft protection ባህሪያትን ለማብራት፦
- ወደ ቅንብሮች
ይሂዱ።
- Google
ሁሉም አገልግሎቶች
የስርቆት ጥበቃ ላይ መታ ያድርጉ።
በሚደገፍ Android መሣሪያ ላይ ባህሪያትን ለማስተዳደር ይህን አገናኝ ይምረጡ።
የስርቆት ማወቂያ መቆለፊያን ያብሩ
የስርቆት ማወቂያ መቆለፊያ የሆነ ሰው ሳይጠበቅ መሣሪያዎን ከወሰደ እና ከሮጠ ለማወቅ ሰው ሠራሽ አስተውሎት፣ የመሣሪያዎን የእንቅስቃሴ ዳሳሾች፣ Wi-Fi እና ብሉቱዝ ይጠቀማል። የስርቆት ማወቂያ መቆለፊያ መሣሪያዎ ከእርስዎ መወሰዱን ካወቀ ይዘቱን ለመጠበቅ በራስ-ሰር የመሣሪያዎን ማያ ገፅ ይቆልፋል። ለምሳሌ፣ የሆነ ሰው ስልኩን ከእጅዎ ላይ ከነጠቀ እና ከሮጠ፣ ብስክሌት ከነዳ ወይም ነድቶ ከሄደ የስርቆት ማወቂያ መቆለፊያ ገቢር ሊሆን ይችላል።
አስፈላጊ፦
- የመሣሪያው ማያ ገፅ ሲቆለፍ የስርቆት ማወቂያ መቆለፊያ ገቢር አይደለም።
- በመደበኛ የመሣሪያ ጥቅም ወቅት መቆራረጦችን ለመገደብ የስርቆት ማወቂያ መቆለፊያ የሚከተሉት ሲሆኑ ላይቀሰቀስ ይችላል፦
- መሣሪያዎ የተረጋጋ የWi-Fi ግንኙነት፣ የብሉቱዝ ግንኙነት ወይም ሁለቱም ሲኖረው።
- በአጭር ጊዜ ውስጥ ተደጋጋሚ መቆለፎች ከነበሩ።
- ስልክዎ ከተሰረቀ ልዩ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ውሂብዎን ለመጠበቅ የስርቆት ማወቂያ መቆለፊያ የስርቆት ሙከራዎችን ለመለየት የመሣሪያ ዳሳሾችን ይጠቀማል።
- የተወሰኑ መደበኛ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች በድንገት ከተወሰደ ስልክ ጋር ተመሳሳይ ባህሪያት ሊኖሯቸው ይችላል። ስልክዎ በደመበኛ አጠቃቀም ምክንያት ከተቆለፈ በቀላሉ ይክፈቱት እና መሣሪያዎን እንደተለመደው መጠቀምዎን ይቀጥሉ። የመደበኛ አጠቃቀም መቆራረጥን ለመቀነስ ባህሪውን ማሻሻል እንቀጥላለን።
የስርቆት ማወቂያ መቆለፊያን ለማብራት፦
- ወደ ቅንብሮች
ይሂዱ።
- Google
ሁሉም አገልግሎቶች
የስርቆት ጥበቃ ላይ መታ ያድርጉ።
- የስርቆት ማወቂያ መቆለፊያ የሚለውን ያብሩ።
- «የስርቆት ማወቂያ መቆለፊያ» ቅንብር ከደበዘዘ መሣሪያዎ ይህን ባህሪ አይደግፍም።
የርቀት መቆለፊያን ያብሩ እና ይጠቀሙ
መሣሪያዎ ከጠፋ ወይም ከተሰረቀ በፍጥነት ማያ ገፅዎን ለመቆለፍ በተረጋገጠ ስልክ ቁጥር የርቀት መቆለፊያ መጠቀም ይችላሉ።
አስፈላጊ፦ የርቀት መቆለፊያን ለመጠቀም የሚከተሉት ሊኖሩዎት ይገባል፦
- የማያ ገፅ መቆለፊያ
- በመሣሪያዎ ላይ ገቢር SIM ካርድ
- የተረጋገጠ ስልክ ቁጥር ያለው መሣሪያ
- ማግኛ ማዕከል በርቷል
- መሣሪያዎ በመስመር ላይ
በርቀት መቆለፊያ በኩል ማያ ገፅ ቁልፍ ሲልኩ መሣሪያዎ ከመስመር ውጭ ከሆነ አንዴ በመስመር ላይ ከሆነ በኋላ ማያ ገፁ በራስ-ሰር ይቆለፋል። የመሣሪያዎ ማያ ገፅ በርቀት ከተቆለፈ በኋላ ሊከፈት የሚችለው በአካባቢው ውስጥ በማያ ገፅ መቆለፊያዎ ብቻ ነው። የመሣሪያው ማያ ገፅ በ24-ሰዓት ጊዜ ውስጥ ሁለቴ በርቀት መቆለፍ ይችላል።
Remote Lock ለማብራት፦
- ወደ ቅንብሮች
ይሂዱ።
- Google
ሁሉም አገልግሎቶች
የስርቆት ጥበቃ ላይ መታ ያድርጉ።
- የርቀት መቆለፊያ ላይ መታ ያድርጉ።
- የርቀት መቆለፊያ የሚለውን ያብሩ።
- ማግበርን ለማጠናቀቅ የተረጋገጠ ስልክ ቁጥር ያስፈልግዎታል።
- ስልክ ቁጥርዎ ካልተረጋገጠ፦
- ቁጥርን አረጋግጥ ላይ መታ ያድርጉ።
- ስልክ ቁጥሮችን በራስ-ሰር አረጋግጥ የሚለውን ያብሩ።
ስልክዎ ከጠፋ ወይም እንደተሰረቀ ከጠረጠሩ፦
- ወደ android.com/lock ይሂዱ።
- ስልክ ቁጥርዎን ያስገቡ።
- የreCaptcha ተግዳሮት ያጠናቅቁ።
- መሣሪያው እንዲቆለፍ ይጠይቁ።
- ከዚያ በአጭር ጊዜ ውስጥ የስልኩ ማያ ገፅ ይቆለፋል።
ጠቃሚ ምክር፦ መሣሪያዎን ከቆለፉ በኋላ የመሣሪያ ውሂብዎን በርቀት ለመጥረግ፣ ደህንነቱን ለመጠበቅ ወይም ለመደምሰስ ወደ ማግኛ ማዕከል መግባት አለብዎት። ማግኛ ማዕከልን እንዴት እንደሚጠቀሙ ይወቁ።
ከመስመር ውጭ መሣሪያ መቆለፊያን ያብሩ
መሣሪያዎ ከመስመር ውጭ ከሆነ በኋላ ከመስመር ውጭ መሣሪያ መቆለፊያ ውሂብዎን ለመጠበቅ በራስ-ሰር የመሣሪያዎን ማያ ገፅ ይቆልፋል። ለምሳሌ፣ የሆነ ሰው ስልክዎን ቢሰርቅ እና ማግኛ ማዕከል በሚለው እንዳያገኙት ለመከላከል በይነመረቡን ቢያጠፋ መሣሪያዎ ከመስመር ውጭ ጥቅም ላይ ከዋለ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ ይቆለፋል።
አስፈላጊ፦
- ስልክዎ የበይነመረብ ግንኙነት ሲያጣ መከፈት አለበት።
- ማያ ገፁ በ24-ሰዓት ጊዜ ውስጥ ሁለቴ በርቀት መቆለፍ ይችላል።
ከመስመር ውጭ መሣሪያ መቆለፊያን ለማብራት፦
- ወደ ቅንብሮች
ይሂዱ።
- Google
ሁሉም አገልግሎቶች
የስርቆት ጥበቃ ላይ መታ ያድርጉ።
- ከመስመር ውጭ መሣሪያ መቆለፊያ የሚለውን ያብሩ።
የማንነት ማረጋገጫን ያብሩ
ማንነትዎን ለማረጋገጥ የማንነት ማረጋገጫ ባዮሜትሪክስ እና ሌሎች መከላከያዎችን ይጠይቃል። ማንነትዎ በመሣሪያዎ ላይ ልዩ ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው ድርጊቶችን ሲያከናውኑ ወይም ከታመኑ ቦታዎች ውጪ ለGoogle መለያዎ ለውጦችን ሲያደርጉ ይረጋገጣል።
አስፈላጊ፦ የማንነት ማረጋገጫ ያላቸው ክፍል 3 ባዮሜትሪክስ የሚደግፉ መሣሪያዎች ብቻ ናቸው። «የስርቆት ጥበቃ» ቅንብሮች ገፁ የማንነት ማረጋገጫን ካልዘረዘረ መሣሪያዎ አይደግፈውም።
የባዮሜትሪክ ማረጋገጫ የሚጠይቁ ልዩ ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው ድርጊቶች
የባዮሜትሪክ ማረጋገጫ የሚከተሉትን ለማድረግ ያስፈልጋል፦
- በGoogle የይለፍ ቃል አስተዳዳሪ የተቀመጡ የይለፍ ቃሎችን እና የይለፍ ቁልፎችን ለመድረስ።
- ከChrome ውጪ ከGoogle የይለፍ ቃል አስተዳዳሪ መተግበሪያዎች ውስጥ የይለፍ ቃሎችን በራስ-ለመሙላት።
- እንደ ፒን፣ ሥርዓተ ጥለት እና የይለፍ ቃል ያለ ማያ ገፅ መቆለፊያ ለመለወጥ።
- እንደ የጣት አሻራ ወይም በመልክ መክፈት ያለ ባዮሜትሪክስ ለመለወጥ።
- የፋብሪካ ዳግም ማስጀመር ለማሄድ።
- ማግኛ ማዕከልን ለማጥፋት።
- ማናቸውንም የስርቆት ጥበቃ ባህሪያት ለማጥፋት።
- የታመኑ ቦታዎችን ለማየት።
- የማንነት ማረጋገጫ የሚለውን ያጥፉ።
- በአሁኑ መሣሪያዎ አዲስ መሣሪያ ለማዋቀር።
- Google መለያ ለማከል ወይም ለማስወገድ።
- የገንቢዎች አማራጮችን ለመድረስ።
ጠቃሚ ምክር፦ በመተግበሪያዎች ውስጥ ለግል ቦታ፣ ለብዙ ተጠቃሚ ሁነታ፣ ለራስ-ሙላ ክፍያዎች ፒን፣ ሥርዓተ ጥለት ወይም የይለፍ ቃሎች መጠቀም መቀጠል ይችላሉ እና የይለፍ ቃል እና ክፍያዎች Chrome ውስጥ በራስ ይሞላሉ።
የGoogle መለያ ጥበቃዎች
ለGoogle መለያዎች ተጨማሪ ደህንነት ለማከል የማንነት ማረጋገጫ መጠቀም ይችላሉ። ይህ ያልተፈቀደለት ሰው በዚህ መሣሪያ ላይ የተገባበትን ማንኛውንም የGoogle መለያ ለመቆጣጠር ይበልጥ ከባድ ያደርገዋል።
«የማንነት ማረጋገጫ» ሲበራ የሚከተሉትን ለማድረግ ባዮሜትሪክስ ያስፈልግዎታል፦
- የይለፍ ቃልዎን ከመለያ ቅንብሮች ላይ ወይም «የይለፍ ቃል ረሳሁ» በሚለው በኩል መለወጥ።
- በመሣሪያው ላይ የመልሶ ማግኛ መስፈርቶችን ማከል ወይም መለወጥ።
የማንነት ማረጋገጫን ለማብራት
- ወደ ቅንብሮች
ይሂዱ።
- Google
ሁሉም አገልግሎቶች
የስርቆት ጥበቃ ላይ መታ ያድርጉ።
- የማንነት ማረጋገጫ ላይ መታ ያድርጉ።
- ለማግበር፦
- ወደ Google መለያ ይግቡ።
- ካላደረጉት ማያ ገፅ መቆለፊያ ያክሉ።
- እንደ የጣት አሻራ ወይም በመልክ መክፈት ያለ ባዮሜትሪክስ ያክሉ።
- እንደ ቤት ወይም ሥራ ያሉ የታመኑ ቦታዎችዎን ያክሉ።
- አማራጭ፦ ይበልጥ በቀላሉ የ Google መለያዎን መልሰው ለማግኘት ስልክ ቁጥርዎን ያረጋግጡ።
- ከማጠናቅቀቅ በኋላ ተከናውኗል ላይ መታ ያድርጉ።
የማንነት ማረጋገጫን ለማጥፋት
- ወደ ቅንብሮች
ይሂዱ።
- Google
ሁሉም አገልግሎቶች
የስርቆት ጥበቃ ላይ መታ ያድርጉ።
- የማንነት ማረጋገጫ ላይ መታ ያድርጉ።
- የማንነት ማረጋገጫ የሚለውን ያጥፉ።
- ማንነትትዎን ለማረገጥ ይጠየቃሉ።
- ከታመኑ ቦታዎችን ውጭ ከሆኑ እርስዎ መሆንዎን በባዮሜትሪክስ ወይም በGoogle መለያዎ ማረጋገጥ ያስፈልግዎታል።
- Google መለያ ከተጠቀሙ፦
- በመሣሪያዎ ላይ «የማንነት ማረጋገጫ» ለማጥፋት Google መለያ ይምረጡ።
- የGoogle መለያውን የይለፍ ቃል ያረጋግጡ።
- የGoogle መለያ የይለፍ ቃል ለመጠቀም አማራጩን ለማግኘት ሌላ መንገድ ይሞክሩ ላይ መታ ያድርጉ።
- ባለ 2-ደረጃ ማረጋገጫን ለGoogle መለያዎ ካበሩ የGoogle መለያ የይለፍ ቃልዎን ካስገቡ በኋላ ሁለተኛ መስፈርት እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ።
ጠቃሚ ምክር፦ በGoogle መለያዎ «የማንነት ማረጋገጫ» ለማጥፋት የበይነመረብ ግንኙነት ያስፈልግዎታል።
ተጨማሪ የስርቆት ጥበቃ ባህሪያትውሂብዎን ከሌቦች እና ካልተፈቀደ መዳረሻ ለመጠበቅ Android የስርቆት ጥበቃ ውሂብዎን ለመጠበቅ የተነደፉ ተጨማሪ አብሮገነብ ባህሪያትን ያካትታል። እነዚህ የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
- ያለተሳካ የማረጋገጫ መቆለፊያ፦ በመሣሪያው ላይ በተጠቃሚ መግቢያዎች ጥበቃ የሚደረግላቸው መተግበሪያዎች ወይም የሥርዓተ ክወና ተግባሮች ውስጥ ሲገቡ ከተከታታይ ያልተሳኩ የማረጋገጥ ሙከራዎች በኋላ የስልክ ማያ ገፅን ይቆልፋል።
- ልዩ ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው ቅንብሮችን ጠብቅ፦ እንደ ማግኛ ማዕከልን ማሰናከል ወይም ማያ ጊዜው አልቋልን ማራዘም ላሉ እርምጃዎች ፒን፣ የይለፍ ቃል ወይም የባዮሜትሪክ ማረጋገጫ በመጠየቅ ልዩ ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው የአስተዳደር ሥራዎች ያልተፈቀደ መዳረሻን ይገድባል።
- የግል ቦታ፦ መተግበሪያዎችን በተለየ ቦታ መደበቅ እና ማዘጋጀት። እንዴት በግል ቦታ ልዩ ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው መተግበሪያዎችን እንደሚደብቁ ይወቁ።
አስፈላጊ፦
- ከእነዚህ ባህሪያት አንዳንዶቹ የሚሠሩት Android 15 እና ከዚያ በላይ ላይ ብቻ ነው። የAndroid ሥሪትዎን እንዴት እንደሚፈትሹ ይወቁ።
- እንደ ያለተሳካ የማረጋገጫ መቆለፊያ እና ልዩ ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው ቅንብሮችን ጠብቅ ያሉ አብሮገነብ ባህሪያት ለተጨማሪ ደህንነት የማያ ገፅ ቁልፍ ይጠይቃሉ። እነዚህ ባህሪያት በነባሪ በርተዋል።
ያልተፈቀዱ ግለሰቦች ለውሂብዎ እና መረጃዎ ቀላል መዳረሻ እንዳይኖራቸው ለማረጋገጥ ስድስት ወይም ከዚያ በላይ አሃዞች ያሉት ጠንካራ ፒን፣ ውስብስብ ቅደም-ተከተል ያለው ሥርዓተ ጥለት ወይም በሌሎች ድር ጣቢያዎች ወይም መተግበሪያዎች ላይ የማይጠቀሙበት የይለፍ ቃል ይጠቀሙ።
ባዮሜትሪክስ የሚጠቀሙ ቢሆን እንኳን ያልተፈቀደለት ግለሰብ ምናልባት የእርስዎን ባዮሜትሪክስ ጥበቃዎች ለመሻር ቢሞክር ጠንካራ የይለፍ ቃል ሊፈልጉ ይገባል። የAndroid መሣሪያ ላይ እንዴት ማያ ገፅ መቆለፊያ እንደሚያቀናብሩ ይወቁ።
እንደ የጣት አሻራ ወይም መልክ ማወቂያ ያለ የባዮሜትሪክ ማረጋገጫ ሁለቱንም ደህንነት እና ምቾት ያቀርባል። ባዮሜትሪክስ ማወቂያ ያላቸው መሣሪያዎች ላልተፈቀደለት ግለሰብ ስልክዎን ለመድረስ ይበልጥ ከባድ ያደርጋሉ እና በተመሳሳይ ጊዜ የተጠቃሚ ልምድ ላይ ጣልቃ አይገቡም። ተጠቃሚዎች ለማረጋገጥ ባዮሜትሪክስ እንዲያዋቅሩ ጠንከር ባለ መልኩ ይበረታታሉ። ለተዘረዘሩ የውቅረት እርምጃዎች ተጨማሪ መረጃ እና እርዳታ ለማግኘት እባክዎ የመሣሪያዎን አምራች ዋቢ ያድርጉ።
ሙሉ በሙሉ የማያምኑት ሰው ጋር መሣሪያን በሚያጋሩባቸው ወይም ይፋዊ ቦታ ውስጥ በሚሆኑባቸው ጊዜያት ይህ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። መሣሪያዎን ለአንድ መተግበሪያ ብቻ ለመቆለፍ ማያ ገፅ ፒን ማድረግ ይችላሉ እና በእርስዎ ፒን ወይም የሥርዓተ ጥለት ወይም የይለፍ ቃል እስከሚነቅሉ ድረስ በዕይታ ውስጥ ይቆያል።
ማያ ገፅ ፒን ሲያደርጉ መሣሪያውን መጠቀም ይችላሉ፣ ነገር ግን ለተመረጠ መተግበሪያ ብቻ። እንዴት ማያ ገፆች ፒን ማድረግ እና መንቀል እንደሚችሉ ይወቁ
በርካታ መተግበሪያዎች እርስዎ የሚከተሉትን ሲያደርጉ ተጨማሪ ደህንነት ያቀርባሉ፦
- ፒን ወይም የይለፍ ቃል ሲያክሉ
- ባዮሜትሪክስ (የጣት አሻራ፣ የመልክ ማወቂያ) ሲጠቀሙ።
- መሣሪያዎን ለመክፈት የሁለት-ደረጃ ማረጋገጫ ሲጠቀሙ።
እንደ ፋይናንስ፣ ክፍያ ወይም ማህበራዊ መተግበሪያዎች ያሉ ልዩ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ወይም አስፈላጊ መረጃ ላላቸው መተግበሪያዎች፣ በደህንነት ወይም የግላዊነት ቅንብሮች ስር የሚያክሏቸውን ተጨማሪ የደህንነት አማራጮች ይፈልጉ።
ለሚደግፏቸው ድር ጣቢያዎች የይለፍ ቁልፎች ያለ የይለፍ ቃል ለመግባት ደህንነታቸው የተጠበቀ መንገዶች ናቸው። እንዴት በይለፍ ቁልፎች ወደ የእርስዎ መተግበሪያዎች እና ድር ጣቢያዎች እንደሚገቡ ይወቁ።
የእርስዎ Android መሣሪያ ከተሰረቀ ወይም መወሰዱን እርግጠኛ ካልሆኑ ውሂቡን በርቀት ማግኘት፣ ደህንነቱን መጠበቅ ወይም መደምሰስ ይችላሉ። ወደ መሣሪያዎ የGoogle መለያ ካከሉ ማግኛ ማዕከል በራስ-ሰር ይበራል።
- በመሣሪያው ላይ ማያ ገፁን መቆለፍ እና ራስዎን ከGoogle መለያዎችዎ ማስወጣት ይችላሉ።
- የማግኛ ማዕከል መተግበሪያውን ወይም ድረ-ገፁን በመጠቀም የመሣሪያዎን አካባቢ ማየት ይችላሉ። እሱን እንደገና ለማግኘት ካልቻሉ ጠፍቷል ብለው ምልክት ሊያደርጉብት ይችላሉ።
- የመሣሪያዎን ውሂብ መደምሰስ እና መሣሪያዎን የፋብሪካ ዳግም ማስጀመር ይችላሉ።
መሣሪያዎ ከመጥፋቱ ወይም ከመሰረቁ በፊት የGoogle መለያዎ ውስጥ መግባትዎን ያረጋግጡ እና የአካባቢ ቅንብርዎ እንደበራ እና ማግኛ ማዕከል እንደነቃ ያረጋግጡ። ማግኛ ማዕከልን እንዴት እንደሚጠቀሙ ይወቁ።
መሣሪያዎን በስርቆት ካጡ መተካት የማይችሉትን አስፈላጊ ውሂብ ጭምር ሊያጡ ይችላሉ። ከዚህ ለመጠበቅ ውሂብዎ ተጠብቆ እንደሚቆይ ለማረጋገጥ የመሣሪያ ምትኬን ማንቃት አለብዎት እና ውሂብዎን ሳያጡ መሣሪያዎን የፋብሪካ ዳግም ማስጀመር ይችላሉ። በእርስዎ Android መሣሪያ ላይ እንዴት ምትኬ ማስቀመጥ እና ውሂብን ወደነበረበት መመለስ እንደሚችሉ ይወቁ።
ስልክዎ ልዩ የመለያ ቁጥር እና በተንቀሳቃሽ ስልክ አውታረ መረብ ከዋኝ የተመደበ ልዩ IMEI ቁጥር አለው። ይህ ለተንቀሳቃሽ ስልክ አውታረ መረብ ከዋኝዎ ምናልባት ስልክዎ ቢጠፋ ለማግኘት ወይም አገልግሎቶችን ለማቆም አጋዥ ሊሆን ይችላል። የተሰረቀ ስልክ ሪፖርት ካደረጉ የሕግ አስከባሪ የመለያ ቁጥርዎን እና IMEI ቁጥርዎን ሊጠይቅም ይችላል። የስልክዎን IMEI ቁጥር እንዴት እንደሚያገኙ ይወቁ።
የIMEI ቁጥርዎን ለማግኘት፦
- ወደ ቅንብሮች
ይሂዱ።
- ስለ ስልክ የሚለውን ይምረጡ።
መሣሪያዎ ከጠፋ ወይም ከተሰረቀ ያልተፈቀደለት ግለሰብ የስልክ ቁጥርዎን ለመቆጣጠር በመሣሪያዎ ውስጥ SIM ካርድዎን ሊጠቀም ይችላል። ሲምዎ ያለ ፈቃድዎ ጥቅም ላይ እንዳይውል ለመከላከል የመሣሪያ ሲምዎን በፒን ይጠብቁ።
መሣሪያዎን በሚያበሩ ማንኛውም ጊዜ ወይም ሲሙ የተለየ መሣሪያ ውስጥ ሲገባ የሲም ፒንዎን ይጠየቃሉ።
የሲም ፒን ለማዋቀር፦
- በእርስዎ Android መሣሪያ ላይ ቅንብሮች
ደህንነት እና ግላዊነት
ተጨማሪ የደህንነት ቅንብሮች ላይ መታ ያድርጉ።
- የሲም መቆለፊያ
ሲም ቆልፍ ላይ መታ ያድርጉ።
ጠቃሚ ምክር፦ አንዳንድ አገልግሎት አቅራቢዎች ለይፋዊ የሚገኝ ነባሪ ፒን አላቸው። ጠንከር ላለ ጥበቃ እሱን መለወጥ ይመከራል።
በማያ ገፅ ቁልፍ ውስጥ ካሉ ማሳወቂያዎች የመጣ መረጃ ያልተፈቀደላቸው ግለሰቦች ውሂብዎን ለመድረስ መጠቀም የሚችሉትን መረጃ ሊሰጣቸው ይችላል። ይህን ለመከላከል በማያ ገፅ ቁልፍ ላይ የሚታየውን የማሳወቂያ ይዘት መቆጣጠር ይችላሉ። Android ላይ እንዴት ማሳወቂያ እንደሚቆጣጠሩ ይወቁ
በማያ ገፅ ቁልፍ ላይ ማሳወቂያ ለመደበቅ፦
- በመሣሪያዎ ላይ ቅንብሮች
ደህንነት እና ግላዊነት
ተጨማሪ የደህንነት ቅንብሮች ላይ መታ ያድርጉ።
- ማያ ገፅ ቁልፍ ላይ ያሉ ማሳወቂያዎች ላይ መታ ያድርጉ።