የላቀ ጥበቃን ሲያበሩ እርስዎ እና መሣሪያዎን ከመስመር ላይ ጥቃቶች፣ ጎጂ መተግበሪያዎች እና የውሂብ ስጋቶች ለመጠበቅ በጣም ጠንካራ የሆኑትን የደኅንነት እና ግላዊነት ባህሪያት ያገኛሉ።
ይህ ባህሪ በርካታ ጥቅማጥቅሞችን ያቀርባል፦
- የምድቡ ምርጥ ጥበቃ፣ አነስተኛ መቆራረጥ፦ የላቀ ጥበቃ ለተጠቃሚ ተስማሚ ለሆነ እና ዝቅተኛ ግጭት ላለው ንቁ መከላከያ ተሞክሮ መሣሪያዎችዎን በAndroid በጣም ውጤታማ የደኅንነት ባህሪያት እንዲያስታጥቁ አማራጩን ይሰጥዎታል።
- ቀላል ማግበር፦ የላቀ ጥበቃ ደኅንነትን ቀላል እና ተደራሽ ያደርጋል። በተሻሻለ ደኅንነት ተጠቃሚ ለመሆን የደኅንነት ባለሙያ መሆን አይጠበቅብዎትም።
- መከላከያ በጥልቀት፦ አንድ ተጠቃሚ አንዴ የላቀ ጥበቃን ካበሩ በኋላ ሥርዓቱ በላቀ ጥበቃ ጥቅል ስር የግለሰብ የደኅንነት ባህሪው በድንገት ወይም ተንኮል-አዘል በሆነ መልኩ እንዳይሰናከል ይከላከላል። ይህ «መከላከያ በጥልቀት» በርካታ የደኅንነት ንብርብሮች አብረው የሚሠሩበት ስልትን ያንፀባርቃል ነው።
- ከመተግበሪያዎች ጋር እንከን የለሽ የደኅንነት ውህደት፦ የላቀ ጥበቃ Chrome፣ Google መልዕክት እና ስልክ በGoogleን ጨምሮ በአብዛኛው የእርስዎ ተወዳጅ የGoogle መተግበሪያዎች ላይ በሙሉ አስፈላጊ የደኅንነት ቅንብሮችን እንደሚያነቃ ነጠላ የመቆጣጠሪያ ነጥብ ይሠራል። እንዲሁም የላቀ ጥበቃ ወደፊት ለማዋሃድ የሚያስቡ የሦስተኛ ወገን መተግበሪያን ያካትታል። ገንቢ ከሆኑ እና መተግበሪያዎች በላቀ ጥበቃ ማዋሃድ ከፈለጉ እንዴት በላቀ ጥበቃ ሁነታ ማዋሃድ እንደሚቻል ይወቁ።
የመሣሪያ ጥበቃን ያብሩ
አስፈላጊ፦- የላቀ ጥበቃ ባህሪውን ከማብራትዎ በፊት ማያ ገፅ መቆለፊያ ያስፈልጋል።
- የመሣሪያ ጥበቃብ ሲያበሩ መሣሪያዎን ዳግም ማስነሳት ሊያስፈልግዎት ይችላል።
- የመሣሪያዎን ቅንብሮች
ይክፈቱ።
- የላቀ ጥበቃ ገፅን ለመክፈት፦
- በቅንብሮች መተግበሪያ በኩል፦
- ደኅንነት እና ግላዊነት ላይ መታ ያድርጉ።
- «ሌሎች ቅንብሮች» ስር የላቀ ጥበቃ ላይ መታ ያድርጉ።
- በGoogle ቅንብሮች በኩል፦
- Google
ሁሉም አገልግሎቶች ላይ መታ ያድርጉ።
- «የግል እና የመሣሪያ ደኅንነት» ስር የላቀ ጥበቃ ላይ መታ ያድርጉ።
- Google
- በቅንብሮች መተግበሪያ በኩል፦
- «የላቀ ጥበቃ» ስር የመሣሪያ ጥበቃ የሚለውን ያብሩ።
- አብራ ይምረጡ።
- በአንዳንድ መሣሪያዎች ላይ አንዳንድ ባህሪያት ለመብራት ዳግም ማስነሳት እንደሚያስፈልጋቸው ለማመላከት «እንደገና እንዲያስጀምሩ ወይም በኋላ እንደገና እንዲያስጀምሩ» ሊጠየቁ ይችላሉ።
- «በኋላ እንደገና ጀምር» የሚለውን ከመረጡ «የላቀ ጥበቃ» ገፅ ስር መሣሪያዎን ዳግም ማስጀመር ይችላሉ። አሁን እንደገና ጀምር ላይ መታ ያድርጉ።
የእርስዎን Google መለያ የላቀ ጥበቃ ውስጥ ለመመዝገብ፦
- «የላቀ ጥበቃ» ስር የመለያ ጥበቃ ላይ መታ ያድርጉ።
- የማያ ገፅ ላይ መመሪያዎችን ይከተሉ።
ጠቃሚ ምክር፦ የላቀ ጥበቃን ካበሩ በኋላ ማያ ገፅ መቆለፊያዎን ካጠፉ ፕሮግራም ገቢር ሆኖ ይቆያል። አንዳንድ ጥበቃዎች በተመቻቸ ሁኔታ ላይሄዱ ይችላሉ እና ስለዚህ ገደብ ለእርስዎ ለማሳወቅ ማስጠንቀቂያ ይታያል።
የመሣሪያ ጥበቃን ያጥፉ
አስፈላጊ፦
- የላቀ ጥበቃ ሲጠፋ አንዳንድ የደኅንነት ቅንብሮችን ለማድህር የመሣሪያ ዳግም ማስነሳት ሊያስፈልግ ይችላል። አንዴ የላቀ ጥበቃ ከጠፋ በኋላ የሸፈናቸው ቅንብሮች እርስዎ ከማብራትዎ በፊት ወደነበራቸው የመጀመሪያ ሁኔታቸው ያድህራሉ።
- የእርስዎን Google መለያ የመለያ ጥበቃ ውስጥ ካስመዘገቡ የመሣሪያ ጥበቃን ካጠፉ በኋላ እንኳን አንዳንድ ጥበቃዎች መብራታቸውን ሊቀጥሉ ይችላሉ። እንዴት ከመለያ ጥበቃ ከምዝገባ መውጣት እንደሚቻል ይወቁ።
- የመሣሪያዎን ቅንብሮች
ይክፈቱ።
- የላቀ ጥበቃ ገፅን ለመክፈት፦
- በቅንብሮች መተግበሪያ በኩል፦
- ደኅንነት እና ግላዊነት ላይ መታ ያድርጉ።
- «ሌሎች ቅንብሮች» ስር የላቀ ጥበቃ ላይ መታ ያድርጉ።
- በGoogle ቅንብሮች በኩል፦
- Google
ሁሉም አገልግሎቶች ላይ መታ ያድርጉ።
- «የግል እና የመሣሪያ ደኅንነት» ስር የላቀ ጥበቃ ላይ መታ ያድርጉ።
- Google
- በቅንብሮች መተግበሪያ በኩል፦
- «የላቀ ጥበቃ» ስር የመሣሪያ ጥበቃ የሚለውን ያጥፉ።
- በባዮሜትሪክስ ወይም ፒን በኩል ያረጋግጡ።
- የመለያ ጥበቃ ላይ ከተመዘገቡ ከማረጋገጥዎ በፊት ቀጥል ላይ መታ ያድርጉ።
- በአንዳንድ መሣሪያዎች ላይ አንዳንድ ባህሪያት ለመጥፋት ዳግም ማስነሳት እንደሚያስፈልጋቸው ለማመላከት «እንደገና እንዲያስጀሩ ወይም በኋላ እንደገና እንዲያስጀሩ» ሊጠየቁ ይችላሉ።
ስለ የላቀ ጥበቃ
በላቀ ጥበቃ የሚቀርቡ ጥበቃዎችን ይገምግሙ።
- መተግበሪያዎች፦
- Google Play ጥቃት መከላከያ፦ ለሁሉም መሣሪያዎች በነባሪ የሚበራው የAndroid አብሮ-ገነብ ተንኮል አዘል ዌር እና ያልተፈለገ የሶፍትዌር ጥበቃ የእርስዎን መተግበሪያዎች እና መሣሪያዎች ለጎጂ ባህሪ ይፈትሻል። የላቀ ጥበቃ ሲበራ ይህ ሊጠፋ አይችልም።
- ያልታወቁ መተግበሪያዎች፦ የላቀ ጥበቃ ካልታወቁ ምንጮች ላይ የመተግበሪያዎች ጭነቶችን ያግዳል። ካልታወቁ ምንጮች የመጡ መተግበሪያዎች ላይገመገሙ ይችላሉ እና ከፍ ያለ የጉዳት ስጋት ሊኖራቸው ይችላል።
- የማህደረ ትውስታ መለያ መስጠት ቅጥያ (MTE)፦ ለሚደገፉ መተግበሪያዎች MTE በራስ-ሰር ይበራል እና መተግበሪያዎች ማህደረ ትውስታን እንዳያበላሹ ይከላከላል።
- የመሣሪያ ደኅንነት፦
- የስርቆት ማወቂያ መቆለፊያ፦ መሣሪያዎ ስርቆትን የሚያመላክት አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ሲያገኝ በራስ-ሰር ይቆልፋል።
- ከመስመር ውጭ መሣሪያ መቆለፊያ፦ የተከፈተ መሣሪያዎ ለረጅም ጊዜ ከመስመር ውጭ ከሆነ በራስ-ሰር ራሱን ይቆልፋል።
- እንቅስቃሴ ያለመኖር ዳግም መነሳት፦ መሣሪያዎ ለ72 ሰዓታት ተቆልፎ ከቆየ በራስ-ሰር ዳግም ያስነሳል። ዳግም የማስነሳት ሂደት አዲስ መክፈት እስከሚከናወን ድረስ የተጠቃሚ ውሂብን የማይነበብ ያደርጋል።
- መልዕክቶች፦
- የአይፈለጌ መልዕክት እና ማጭበርበር ጥበቃ፦ የGoogle መልዕክቶች የአይፈለጌ መልዕክት እና ማጭበርበር ጥበቃ የማይፈለጉ እና ጎጂ ሊሆኑ የሚችሉ መልዕክቶችን እንዲለዩ እና እንዲያስወግዱ ያግዙዎታል።
- ደኅንነታቸው ያልተጠበቀ አገናኞች፦ የላቀ ጥበቃ ሲበራ Google መልዕክቶች ውስጥ ካልታወቁ ተጠቃሚዎች ስለተላኩ አገናኞች ማስጠንቀቂያዎች ይደርሱዎታል። ይህ የማስገር ሙከራዎ እና ተንኮል-አዘል ድር ጣቢያዎችን እንዲያስወግዱ ያግዝዎታል።
- አውታረ መረብ፦
- የ2G አውታረ መረብ ጥበቃ፦ ለሚደገፉ መሣሪያዎች የላቀ ጥበቃ ሲበራ መሣሪያዎ ያነሰ ደኅንነት እንዳላቸው ከሚታሰቡ 2G አውታረመረቦች ጋር ከእግዲህ አይገናኝም።
- ስልክ በGoogle፦
- የደዋይ መታወቂያ እና አይፈለጌ መልዕክት፦ ስልኩን ከማንሳትዎ በፊት እንኳን ስልክ በGoogle ውስጥ የታወቁ የአይፈለጌ መልዕክት ቁጥሮችን ይለዩ።
- ራስ-ሰር ጥሪ ማሳያ፦ በሚደገፉ ክልሎች ውስጥ ስልክ በGoogle ውስጥ ሰው ሠራሽ አስተውሎት ረዳት ገቢ ጥሪዎችዎን ያጣራል እና እንደ አይፈለጌ መልዕክት የተለዩትን በራስ-ሰር አይቀበልም።
- ድር፦
- Android ደኅንነቱ የተጠበቀ አሰሳ፦ በፍጥነት እየመጡ ካሊ ተንኮል-አዘል ድር ጣቢያዎች ላይ የማስገር ጥቃቶችን ለመከላከል Android ደኅንነቱ የተጠበቀ አሰሳ Live የስጋት ጥበቃ ይነቃል።
- Chrome ማሰስ፦ ይበልጥ ደኅንነቱ የተጠበቀ አሰሳን ለማረጋገጥ Chrome ይህን ማድረግ ሲቻል ለሁሉም የድር ጣቢያ ግንኙነቶች በራስ-ሰር የኤችቲቲፒኤስ አጠቃቀምን ያስፈጽማል።
- ጃቫስክሪፕት ጥበቃዎች፦ ጃቫስክሪፕት አትቢው Chrome ውስጥ ይጠፋል፣ ይህም ሊኖር የሚችል የደኅንነት ተጋላጭነትን ይቀንሳል።