Jump to content

ናዋትል

ከውክፔዲያ

ናዋትል (nāhuatl, mexìcatlàtōlli, Nawatl) በኡቶ-አዝቴካዊ የቋንቋ ቤተሠብ የሚከተት በሜክሲኮ ኗሪዎች የሚናገር ቋንቋ ነው። በተለይ እስፓንያውያን16ኛው መቶ ዘመን ከወረሩ አስቅደሞ በጣም ትልቅና መደበኛ ቋንቋ ሆኖ ነበር። እስከ ዛሬ ግን በ1.5 ሚሊዮን ኗሪዎች በሜክሲኮ እየተናገረ ነው። የዛሬውኑ ናዋትል ከስፓንኛ ታላቅ ተጽኖ ተቀብሏል። ኣብዛኛው ተናጋሪዎቹ ስፓንኛ ደግሞ የሚችሉ ናቸውና።

ጥንታዊ መጽሐፍ በዱሮ ናዋትል ስዕል-ጽሕፈት

ስፓንያውያን በደረሡ ጊዜ ናዋትል የራሱ ጽሕፈት ነበረው። ይህ ጽሕፈት እንደ ጥንታዊ ግብጽ ስዕል ጽሕፈት ይመስል ነበር። ነገር ግን እነዚህ ጽሑፎች በአብዛኛው በካቶሊኮች ስለ ተቃጠሉ፣ ዛሬ ቋንቋው የሚጻፈው በላቲን ፊደል (አልፋቤት) ሆኗል።

በናዋትል ሰዋስው አያሌ ባዕድ መነሻዎችና መድረሻዎች አንድላይ ሊቀጣጥሉ ይችላሉ። ስለዚህ አንድ ቃል እጅጉን እንዲረዝም ተችሏል።

አንዳንድ ቃል በስፓንኛና በእንግሊዝኛ አማካኝነት በአለሙ ቋንቋዎች በሰፊ ይገኛሉ። ለምሳሌ የሚከተሉት የአማርኛ ቃላት መጀመርያቸው እንዲያውም ከናዋትል ቃላት ነበሩ፦

'ቸኮላታ' - ከ Xocolatl (ሾኮላትል)
'ቲማቲም' - ከ Tomatl (ቶማትል)
'ካካዎ' - ከ Kakawatl (ካካዋትል)
'አቡካዶ' - ከ Ahuacatl (አዋካትል)

የናዋትል ቋንቋ ምሳሌዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
Tlanextili - (ትላነክስቲሊ) - ደህና አደሩ?
Chotlakili - (ቾትላኪሊ) - ደህና ይመሹ።
Kinejki tinemi? - (ኪነይኪ ቲነሚ?) - እንደምን ነዎት?
Qualtzin ninemi - (ኳልጺን ኒነሚ) - ደህና ነኝ።
Tlaxtlaui - (ትላክስትላዊ) - አመሰግናለሁ።
Wikipedia
Wikipedia