የእርስዎን የYouTube ሰርጥ ይሰርዙ ወይም ይደብቁ

በሰርጥዎ ላይ ያለውን ይዘት ለጊዜው ለመደበቅ ወይም ሰርጥዎን በቋሚነት ለመሰረዝ መምረጥ ይችላሉ።

How to hide or delete your YouTube channel

የቅርብ ጊዜ ዜና፣ ዝማኔዎች እና ጠቃሚ ምክሮችን ለማግኘት ለYouTube ተመልካቾች ሰርጥ በደንበኝነት ይመዝገቡ።

ሰርጥዎን ለጊዜው ይደብቁ

ይዘትን ከእርስዎ YouTube ሰርጥ ላይ መደበቅ እና በኋላ ላይ እንደገና ለማንቃት መምረጥ ይችላሉ። ሰርጥዎን መደበቅ የሰርጥ ስምን፣ ቪድዮዎችን፣ መውደዶችን፣ የደንበኝነት ምዝገባዎችን እና የደንበኝነት ተመዝጋቢዎችን የግል ያደርጋቸዋል። በተጨማሪ የእርስዎ የዕይታ ቆጠራዎች ትክክል ላይሆኑ ይችላሉ። ሰርጥዎን እንደገና ካነቁ በኋላ እነዚህ ቆጠራዎች እስኪዘምኑ እስከ አንድ ሳምንት ድረስ ሊወስድ ይችላል።

ሰርጥዎን ወይም የሰርጥዎን ይዘት ይደብቁ፦

  1. ወደ YouTube ስቱዲዮ በመለያ ይግቡ።
  2. ከግራ ጎን አሞሌው ላይ ቅንብሮች «» ይምረጡ።
  3. ሰርጥ እና ከዚያ የላቁ ቅንብሮች የሚለውን ይምረጡ።
  4. ግርጌው ላይ የYouTube ይዘትን አስወግድ የሚለውን ይምረጡ።
    1. ማስታወሻ፦ ይህ አገናኝ ሰርጥዎን መሰረዝ ወይም መደበቅ ወደሚችሉበት ገፅ ይወስድዎታል። የመግቢያ ዝርዝሮችዎን እንዲያስገቡ ሊጠየቁ ይችላሉ።
  5. ሰርጤን መደበቅ እፈልጋለሁ የሚለውን ይምረጡ።
  6. በሰርጥዎ ላይ ምን እንደሚደበቅ ለማረጋገጥ ሳጥኖቹን ይምረጡ።
  7. ሰርጤን ደብቅን ይምረጡ።

ይዘትዎ ለሌሎች እንዲታይ ማድረግ ከፈለጉ ወይም ለመስቀል፣ አስተያየት ለመስጠት ወይም አጫዋች ዝርዝሮችን ለመጠቀም ከፈለጉ፣ ሰርጡን እንደገና ማንቃት ይችላሉ።

ሰርጥዎን በቋሚነት ይሰርዙ

የYouTube ሰርጥዎን መዝጋት ቪዲዮዎችን፣ አስተያየቶችን፣ መልዕክቶችን፣ አጫዋች ዝርዝሮችን እና ታሪክን ጨምሮ ይዘትዎን እስከመጨረሻው ይሰርዘዋል። በአሁኑ ጊዜ በተንቀሳቃሽ መሳሪያዎች ላይ አንድ ሰርጥ መሰረዝ እንደማይችሉ ልብ ይበሉ።

ሰርጥዎን እስከመጨረሻው ለመሰረዝ የሚመርጡ ከሆነ መለያዎን መልሰው እንዲያገኙ ለማድረግ ልንቸገር እንችላለን።

የYouTube ሰርጥዎን ይሰርዙ፦

  1. ወደ YouTube ስቱዲዮ በመለያ ይግቡ።
  2. ከግራ ጎን አሞሌው ላይ ቅንብሮች «» ይምረጡ።
  3. ሰርጥ እና ከዚያ የላቁ ቅንብሮች የሚለውን ይምረጡ።
  4. ግርጌው ላይ የYouTube ይዘትን አስወግድ የሚለውን ይምረጡ። ከተጠየቁ የእርስዎን በመለያ መግቢያ ዝርዝሮች ያስገቡ።
  5. ይዘቴን በቋሚነት መሰረዝ እፈልጋለሁ የሚለውን ይምረጡ።
  6. ሰርጥዎን መሰረዝ እንደሚፈልጉ ለማረጋገጥ ሣጥኖቹን ይምረጡ።
  7. የእኔን ይዘት ሰርዝ የሚለውን ይምረጡ።

ሰርጥዎ በቋሚነት እስከሚሰረዝ የተወሰነ ጊዜ ሊወስድ ይችላል። በአጭር ጊዜ ውስጥ የቪድዮዎችዎን ጥፍር አከሎች በጣቢያው ላይ ማየት መቀጠል ይችሉ ይሆናል።

ማስታወሻ፦ እነዚህ እርምጃዎች የYouTube ሰርጥዎን ብቻ ይሰርዛሉ እንጂ ለመግባት የሚጠቀሙበት Google መለያዎን አይሰርዙም። የእርስዎን አጠቃላይ Google መለያ እንዴት መሰረዝ እንደሚችሉ ይወቁ።

አንድን ሰርጥ ከሰረዙ በኋላ የሰርጡ ዩአርኤል እና የሰርጥ ስም ከእንግዲህ በYouTube ትንታኔ ውስጥ አይታዩም ወይም ሊፈለጉ አይችሉም። እንደ የእይታ ጊዜ ያለ ከሰርጡ ጋር የተጎዳኘ ውሂብ አሁንም የድምር ሪፖርቶች አካል ይሆናል፣ ነገር ግን ለተሰረዘው ሰርጥ አይቆጠርም።

ይሄ አጋዥ ነበር?

እንዴት ልናሻሽለው እንችላለን?

ተጨማሪ እገዛ ያስፈልግሃል?

እነዚህን ቀጣይ እርምጃዎች ይሞክሩ፦

ፍለጋ
ፍለጋ አጽዳ
ፍለጋን ዝጋ
ዋናው ምናሌ
9679292682657437144
true
የእገዛ ማዕከልን ይፈልጉ
false
true
true
true
true
true
59
false
false
false
false